Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ ዘገባዎች

The Africa Report

  • ሱዳን በ አባይ ግድብ መሙላት ላይ ኢትዮጵያን ሀላፊነቷን የሚገልጽ ሀሳብ እንድጸጥ መጠየቋን ነው የጻፈው።
  • የኢትዮጵያ አወዛጋቢው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ዳይሬክተር ክፍሌ ሆሮ በቅርቡ የሰጡት መግለጫ የሱዳንን ፍላጎትና ጥያቄ ዙርያ ኢትዮጵያ ያላትን ሃላፊነት ያላማከለ እንደሆነ መቃወሟን ነው የገለጸው።
  • ኢትዮጵያን ባለፈው ሳምንት ለአል አረቢያ ቲቪ በሰጠችው መግለጫ ምንም እንኳን በታችኛው የተፋሰሱ አገሮች በግድቡ ሙሌት ላይ ምንም ዐይነት ውሳኔ መወሰን እንደማይችሉ የሚገልጽ እንደሆነ በማንሳት ያላት ቅሬታ እያሰማች እንደሆነ አድርጎ ነው የገለጸው።

ሊንክ፟-  https://www.theafricareport.com/210075/sudan-calls-out-ethiopia-for-irresponsible-comments-on-filling-of-the-gerd/

Foreign Affairs           

  • ትግራይ ላይ በሚደርገው የዘር ማጽዳት አለም  ችላ ማለት አይችልም በሚል ሀሳብ ለህወሓት ያለውን ድጋፍ በግልጽ ያሳየ ጽሁፍ ነው ።
  •  ከአንድ አመት ተኩል በላይ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ /የትግራይ ክልል ውስጥ በስፋት ያልታየ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሲካሄድ እንደቆየ አድርጎ የህወሓት ሀይሎች ” የዘር ጭፍጨፋ ተካሂዶብናል” የሚሉትን ሀሳብ በሚደግፍ መልኩ የዓለምን ማህበረሰብ ለማሳመን የቀረበ ፕሮፓጋንዳ ነው።
  • ነገር ግን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና የሂዩማን ራይትስ ዎች መርማሪዎች እንዳሳዩት ጭካኔው ቀጥሏል የሚል መረጃ ሲያወጡ የነበሩና በህወሐትም መሪዎች በትግራይ አሰቃቂ ግፍ እየደረሰ መሆኑን ህዝቡ እራሱ መረጃዎችን እያወጣ እንደሆነ ተመልክተናል።

ሊንክ – https://www.foreignaffairs.com/articles/ethiopia/2022-06-02/ethiopias-invisible-ethnic-cleansing

All Africa

  •  ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ  ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መፈለጋቸውን  የሚተነትን ነው።
  • የኡጋንዳ እና የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ከቀጠናዊ ጸጥታ፣ ቅንጅት ማሳደግ እና በሁለቱ እህትማማች ሀገራት መካከል ያለውን ምርታማ ግንኙነት እና አጋርነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ ያሳያል ።
  • እንደ ፓን አፍሪካኒስት ኢትዮጵያ እየወሰደች ባለው ልማታዊ አቅጣጫ በጣም የሚያኮራና የአፍሪካን ህዝቦች ቀጣናዊ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በተመለከተ የጋራ ራዕይ እንጋራለን። ይህ ግንኙነት እና አጋርነት ሊቀጥል ይገባል በሚል አጋርነታችን መቀጠል እንዳለበት መነጋገራቸውን ነው የነገረን።

ሊንክ  https://allafrica.com/stories/202206020096.html

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *