የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ሕዳር 5፣ | 2015 ዓ.ም – Nov 14 | 2022
Foreign Policy
- የኢትዮጵያ አደገኛ የሰላም መንገድ የሚል ርዕስ ተሰቶት የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- አሁን የተጀመረው የሠላም ስምምነት በኢትዮጵያ ለሁለት ዐመታት የተካሄደውን ጦርነት የሚያስቆም እንደሆነ
- የሠላም ስምምነቱ ጠንካራ እንዳልሆነ
- የሠላሙ ስምምነት ውጤታማ እንዳይሆን የሚያደርጉ አንዳንድ የፖለቲካ ጉዳዮች እንዳሉ።
- በጦርነቱ የትግራይ ክልል ከመብራት ፣ ኢንተርኔትና ባንክ አገልግሎቶች ተቋርጦ እንደነበር።
- ስምምነቱ በዋንኝነት የትግራይን ህዝብ የሚጠቅም እንደሆነ
- የኤርትራ መንግስት ምላሽም የሠላም ድርድሩን ውጤታማነት የሚያደናቅፍ እንደሆሚሆን የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://foreignpolicy.com/2022/11/14/ethiopia-war-peace-deal-truce-tigray-humanitarian-crisis/
Forbes
- ፍትህና ተጠያቂነት ከሌለ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ሊኖር አይችልም የሚል ድምዳሜን በርዕሱ የያዘ ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- በቅርቡ በመንግስትና በህወሓት መካከል የተደረገው ስምምነት የወነጀለኞች ተጠያቂነትን ያላካተተ በመሆኑ ለውጤታማነት የሚያበቃውን ተዓማኒነት ያላገኘ ስምምነት እንደሆነ
- በጦርነቱ በሁሉም ወገኖች የተፈጸሙ ወንጀሎች ተመርምረው ውንጀለኞች ለህግ መቅረብ እንዳለባቸው።
- በኖቬምበር 2022 መጀመሪያ ላይ የዶ/ር ዴኒስ ሙክዌጅ ፋውንዴሽን “በኢትዮጵያ ከግጭት ጋር የተያያዙ ወሲባዊ ጥቃቶችን መረዳት” የሚለውን አዲሱን ሪፖርታቸውን እንዳሳተሙ
- ሪፖርቱ እንዳመለከተው “የኢትዮጵያ እና አጋር ኃይሎች የትግራይ ተወላጆችን ለማስወገድ እና/ወይም በግዳጅ ለማፈናቀል በሰፊው ተንቀሳቅሰው ወንጀል እንደፈጸሙ መረጃዎች እንዳሉት
- ሪፖርቱን አሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም እገዛ በማድረግ እንዳሠሩት
- የኤርትራ ወታደሮችም በትግራይ ህዝብ ላይ የወሲብ ጥቃትን ጨምሮ በብሔር የበቀል እርምጃዎች ወስደው እንደነበር ከጥቃቱ ከተረፉ ሠዎች መሰማቱ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.forbes.com/sites/ewelinaochab/2022/11/13/there-can-be-no-peace-in-ethi
Global Times
- በኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት ግጭት ለማቆም የደረሱበትን ስምምነት ለመፈጸም ቁርጠኛ እንደሆኑ የሚያብራራ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የደቡብ አፍሪካውን ስምምነት ለማስፈጸም እንዲረዳ በናይሮቢ ሌላ አጋዥ ስምምነት እንደተፈራረሙ
- የአፍሪካ ህብረትም እስካሁን ድረሥ የሠላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት እንንዲኖረው ከፈተኛ ድርሻ እየተጫወተ እንደሚገኝ።
- የንጹሀንን ጥበቃና የእርዳታ ሠራተኞች ጥበቃን የሚያቀላጥፍ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ለመሥራት እንደተስማሙ
- ባስቸኳይ ተፈጻሚ መሆን እንዳለበትም የአፍሪካ ህብረቱ ሉዩ ልዑክ አደራዳሪው ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ለሚዲያ መግለጻቸው
- ሁለቱም ካላት ሠላምን ለማምጣት ያለው መፍትሔ ስምምነቱን መፈጸም ብቻ እንደሆነ መስማማታቸው የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.globaltimes.cn/page/202211/1279419.shtml