የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም 11፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 21 | 2022
BBC
- የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን የህወሓት ሀይል መግለጹን የሚተነትን ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ከፍተኛ ጥቃት ፈጽመዋል ሲሉ የትግራዩ አማፂ ቡድን የህወሓት ቃል አቀባይ መግለፁን ።
- የአሜሪካ ተወካይ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ሲሻገሩ አሜሪካ ማውገዞን ።
- በዚህ ጉዳይ ላይ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መንግስታት እስካሁን የሰጡት አስተያየት አለመኖሩን ።
- ኤርትራ በህወሓት ላይ እየወሰደች ያለችው ጥቃት ከተረጋገጠ ባለፈው ወር ለአምስት ወራት የተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት መፈራረስን ተከትሎ መባባሱን ።
- ግጭቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀሰቀሰው በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ክልሉን በሚቆጣጠረው ህወሓት መካከል የተፈጠረውን ከፍተኛ ፍጥጫ ተከትሎ እንደሆነ ።
- ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር በመሆን ጣልቃ ገብታ የነበረ ቢሆንም ባለፈው አመት አብዛኛውን ወታደሮቿን ማስወጣቷ መዘገቡን ።
- የሕወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ እና በኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን መናገራቸውን ።
ሊንክ https://www.bbc.com/news/world-africa-62957817
Aljazeera
- የህወሓት ሃይሎች የኤርትራ ወታደሮች ጥቃት ሰንዝራለች ሲሉ መክሰሳቸውን የህወሓት የአቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ ያስተጋባ ጽሁፍ ነው።
የተነሱነጥቦች
- በህወሓት ሃይሎች ኤርትራ ሙሉ ጥቃት እንደከፈተች እና በድንበር አካባቢ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን መግለፃቸውን ።
- ጦርነቱ ለሁለት አመታት መቆየቱ ቢታወስም አሁን ላይ ዳግም የጀመረውን ጦርነት እይተባባሰ መምጣተን ።
- ኤርትራዊያን ወታደሮች ከኢትዮጵያ ፌዴራል ሃይሎች ጋር በመተባበር የህወሓትን ሀይሎች እይተዋጉ እንደሆነ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ መግለፃቸውን ።
- የህውሓት ሀይል እንደሚለው የኤርትር ወታደሮች ሙሉ ሰራዊቷን እና የተጠባባቂ ሃይሎችን እያሰማራች እንደሆነ ።
- የህወሓት ቃል አቀባይ እንዳሉት የህወሓት ሀይሎችም በጀግንነት ቦታቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ ማለታቸውን አቶ ጌታቸው ረዳ መናገራቸውን በትዊተራቸው ላይ ማስቀመጣቸውን ።
- በፊደራል መንግስትም ሆነ በኤርትራ መንግስት ምንም አይነት መግለጫ አለመኖሩን ።
- ሁለት የረድኤት ሰራተኞች በድንበር አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ መደረጉን እና ለተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ መተኮስን ጨምሮ እንደዘገበው ሮይተርስ የዜና ወኪል መዘገቡን ።
- በተጨማሪም ጦረነቱ የት አካባቢ እንደሆነ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ መሬት ላይ ስለመሆኑ የገለጹት ነገር አለመኖሩን ።
ሊንክ https://www.aljazeera.com/news/2022/9/20/tigrayan-forces-accused-eritrea-starting-offensive-
VOA
ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን ወንጀል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣውን ሪፖርት ውድቅ ማደረጉን ለማብራራት የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በጦርነት በምትታመሰው ትግራይ ክልል በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም ሊፈፀሙ እንደሚችሉ የሚገልጽ የተባበሩት መንግስታት መርማሪዎች ያቀረቡትን ዘገባ መንግስት ውድቅ እንዳደረገ ።
- የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ከሁለት አመት በፊት በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በሁሉም ወገኖች የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያሳይ ማስረጃ ማግኘቱን ማስታወቁን ።
- የኖቤል ተሸላሚ የሆነው መንግስት እና አጋሮቹ 6 ሚሊዮን የትግራይን ክልል ለሆነችው ዕርዳታ በመከልከላቸው ከፍተኛ ስቃይ ሲፈጽሙባቸው እንደነበረ ።
- ከኮሚሽነሯቿ አንዷ የሆነችው ካአሪ ቤቲ ሙሩንጊ በበኩላቸው እንደተናገሩት የምግብ፣ የመድሃኒት እና የመሰረታዊ አገልግሎቶች እና በሲቪል ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ማለታቸውን ።
- ኮሚሽነሯ እንደተናገሩት የፌዴራል መንግስት ረሃብን እንደ ጦርነት ዘዴ እየተጠቀመ ነው ብለን የምናምንበት ምክንያታዊ ምክንያቶች አሉን ስትል መናገሯን ።
ሊንክ https://www.voanews.com/a/ethiopia-rejects-un-report-warning-of-crimes-against-hu