የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
መስከረም 5፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 15 | 2022
VOA
- በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የአየር ድብደባ ድሮኖች ጥቅም ላይ መዋላቸውን የህወሓት ሀይሎች መናገራቸውን በዝርዝር የሚተነትን ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በመንግስት እና ህወሓት የእርስ በርስ ጦርነት እየተቀጣጠለ ባለበት ወቅት በመቀሌ ዋና ከተማ የሚገኘው ሆስፒታል ላይ ጥቃት መድረሱን
- የሆስፒታሉ ሀላፊ እንደተናገሩት በጥቃቱ አስር ሰዎች መሞታቸውን መናገራቸውን ዘገባው ዘግቦል ።
- የህወሓት ሀይሎች እና የሆስፒታሉ ዶክተሮች የኢትዮጵያ መንግስት ለመጨረሻዎቹ ጥቃቶች ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እየተጠቀመ ነው ማለታቸውን ።
- ጥቃቱ እስካሁን ያደረሰው ጉዳት በሆስፒታሉ ያሉ ሰዎችንም እየጎዳ እንዳለ የሆስፒታሉ ሀላፊ የሆኑት ደ/ር ክብሮም ሀይለስላሴ መናገራቸውን ዘገባው ገልፁል
- አሁን ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሆስፒታሉ ላይ የቀዶ ጥገና እያደረጉ መሆናቸውን ባለስልጣኑ መናገራቸውን
ሊንክ https://www.voanews.com/a/tigray-s-leadership-says-drones-used-in-ethiopia-s-latest-
France24
- በኢትዮጵያ ትግራይ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት 10 ሰዎች እንደተገደሉ የሚተነትን ጽሁፍ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በመቀሌ ከተማ እሮብ እለት በነበረው ጦርነት የአስር ሰዎች ሒወት ማለፉን ።
- ይህ ጦርነት የተከሰተው የተኩስ አቁም ስመምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ እንደሆነ መናገራቸውን ዘገባው ዘግቦል ።
- በመቀሌ ላይ ለሁለተኛ ቀን በቀጠለው የአየር ድብደባ 10 ሰዎች መሞታቸውን።
- አሰር ሰዎች መሞታቸውን የሆስፒታሉ ባለስልጣናት የገለጹ መሆኑን።
- ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ዳግም የፌደራል መንግስት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ ነኝ ማለቱን ።
- የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተፋላሚዎቹ ወገኖች የሰላም ዕድልን እንዲጠቀሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ዳግም ጦርነቱ መቀስቀሱን ።
- የዚው ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ሀኪም ፋሲካ አምደስስላሴ የሟቾችን ቁጥር ማረጋገጣቸውን ።
- በመጀመሪያው የቦምብ ጥቃት ሁለት ሴቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ሁለተኛ አድማ ዳግሞ ተጎጂዎችን ለመርዳት በተሰበሰበው ህዝብ ላይ እንደሆነ ።
ሊንክ https://www.france24.com/en/live-news/20220914-10-killed-in-twin-air-strikes-on-ethiopia-s-
Al-Arabiya
- የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ ነኝ ማለቱን የሚያብራራ ጽሁፍ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ።
- ጦርነቱ ለሁለት ዓመታት ግጭት እንዲቆም መንግስት ቁርጠኝነቱን እንዳለው ።
- የህወሓት ሀይሎች ለመደራደር ዝግጁ ነን ካሉ በኋላ የመጀመሪያ የሕዝብ አስተያየት ምን ይህን ።
- ሚኒስቴሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት ልኡካን ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ አቋም እንዳለው።
- ሚኒስተሩ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ በተስፋ መግለፃቸውን ።
ሊንክ https://english.alarabiya.net/News/world/2022/09/14/Ethiopia-government-says-committed-to-