የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም 3፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 13 | 2022
Reuters
- የህወሓት ሃይሎች የተኩስ አቁሙን በመተው ወደ ሰላም መምጣታቸውን አሜሪካ በደስታ መቀበሏን ነው የሚገልጸው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የህወሓት ሃይሎች የአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደሚቀበሉ የገለፁትን መግለጫ በደስታ እንደሚቀበል የአሜሪካ መንግስት መናገሩን ።
- የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ካሪን ዣን ፒየር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሁለቱም ወገኖች ጦርነታቸውን አቁመው ወደ ውይይት የሚመለሱበት ጊዜ አሁን ነው ማለታቸውን ።
- መንግስት ይህንን ጊዜ ተጠቅሞ ለሰላም ዕድል መስጠት እንዳለበት መናገራቸውን
- በተጨማሪም አሜሪካ አሁን ላይ ኤርትራም ሆነች ሌሎች ሀገራት ከህወሓት ጋር ያለውን ግጭት ማስቀረት አለባቸው ስትል መናገሯን ።
ሊንክ https://www.reuters.com/world/white-house-welcomes-tigrayan-forces-openness-ceasefire-
* በተጨማሪም ሮይተርስ እንደዘገበው በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ስምምነትን ተከትሎ የአየር ጥቃት እንደደረሰ የሚዘግብ ።
የተነሱ ሀሳቦች
- በመቀሌ ማክሰኞ በደረሰ የአየር ጥቃት ቢያንስ አንድ ሰው መቁሰሉን ።
- የአየር ድብደባው የደረሰው የህወሓት ሃይሎች ከፌደራል መንግስት ጋር የተኩስ አቁም ለማድረግ ዝግጁ ነን ካሉ ከሁለት ቀናት በኋላ መሆኑን ።
- የአየር ድብደባው በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እና በክልሉ ሀይል በሚተዳደረው ድምፀወያኔ ቲቪላይ ጉዳት ማድረሱን ።
- ሰዎች እንደቆሰሉ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ክብሮም ገብረስላሴ መናገራቸውን ።
- የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የንግድ ካምፓሱ በሰው አልባ አውሮፕላን መመታቱን ።
- የኢትዮጵያ ጦር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ እና የመንግስት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸውን ።
The Africa report
ሀጎስ ገብረአምላክ በሚባለው ግለሰብ እንደተፃፈው የህውሓትን ጦርነት እንደገና ለማስጀመር የኤርትራ ምን አይነት ሚና ተጫውታለች የሚለውን ትንታኔ የሚዘግብ ።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት እና በህወሀት ሀይሎች መካከል ለሳምንታት ከዘለቀው ፍጥጫ በኋላ የተቀሰቀሰው የህወሓት ጦርነት ለአጭር ጌዜ እርቅ መፈጠሩን በድጋሚ መቀጥሉን ።
- ህወሓት የኤርትራ መንግስት ወታደሮቹን ወደ ጦርነት ልኳል ሲል መክሰሱን ።
- የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ የኤርትራ ኤምባሲ በተከፈተበትን የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቁልፍ መቀበላቸውን ።
- የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኤርትራ ኤምባሲ በተከፈተበትን የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ቁልፍ መቀበላቸውን ።
- የኤርትራ ጦር መሬት ላይ ያለው ተሳትፎ በህወሓት ሀይሎች ተቋማት ላይ የሚደረግ ወረራ ብቻ እንደሆነ ።
- በህወሓት እና በኤርትራ መካከል ያለው እስካሁን መሬት ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት እንደሌለ ።
- በኤርትራ አዋሳኝ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ አካባቢዎች ድንበር ተሻጋሪ የጦር መሳሪያ የተኩስ እና የወታደር እንቅስቃሴ መስተዋሉን ።
ሊንክ https://www.theafricareport.com/239656/eritreas-role-in-resumption-of-tigrays-war/
Aljazeera
የአየር ጥቃት በመቀሌ መድረሱን እና በአይደር ሆስፒታል በሰራተኞች ላይ የደረሰ ጉዳት ።
የተነሱ ነጥቦች
- በትግራይ ክልል የአይደር ሆስፒታል ኃላፊ የሆኑት አቶ ክብሮም ገብረስላሴ በጥቃቱ አንድ ሰው እንደቆሰለ መናገራቸውን ።
- የአየር ድብደባው የደረሰው የህወሓት ሃይሎች ከፌደራል መንግስት ጋር የተኩስ አቁም ለማድረግ ዝግጁ ነን ካሉ ከሁለት ቀናት በኋላ መሆኑን ።
- የአየር ድብደባው በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እና በክልሉ ሀይል በሚተዳደረው ድምፀወያኔ ቲቪላይ ጉዳት ማድረሱን ።
- ሰዎች እንደቆሰሉ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ክብሮም ገብረስላሴ እና የአይን እማኞች መናገራቸውን ።
- ከህወሓት ሀይሎች ጋር እየተዋጋ ያለው የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ምንም አይነት አፋጣኝ አስተያየት አለመስጠቱን ።
- የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የቢዝነስ ካምፓሱን በሰው አልባ አውሮፕላኖች መመታቱን መንግስትን እንዲ በማለት መክሰሳቸውን አስቀምጠዋል ።
ሊንክ https://www.aljazeera.com/news/2022/9/13/air-strike-hits-capital-of-ethiopias-northern-tigray-