የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ነሐሴ 30 ፣ | 2014 ዓ.ም – SEP 5 | 2022
VOA
- በኢትዮጵያ ሌሎች አካባቢ ከሚታየው ሁከት በስተጀርባ ያለው ምንድን ነው የሚል የቪዲዮ መረጃ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በጋምቤላ ክልል ሰኔ ላይ በተነሳው ግጭት የሸኔ ሀይል ጥቃት ማድረሱ
- በወቅቱ ሸኔ ባስነሳው ግጭት በሀገሪቱ ላይ ተጨማሪ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይስፋፋ ስጋት መፍጠሩ
- እንደተናገረው በተለያዩ አካባቢዎች ለምሳሌ በአዲስአበባ እና አዳማ ሰዎች እየታሰሩ እና እየሞቱ እንደሆነ ጋዜጠኞችና እን ዊሊያም ዲቪሰን የሚባሉ ግለሠቦችን መናገራቸው
- ነገር ግን አሁን የጋምቤላ ክልል የሰላም እና የደንነት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ቻንኮት ቾቲ እንደተናገሩት አሁን ላይ ያለው እውነታ ሰላም እና የተረጋጋች መሆኑን የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው
ሊንክ https://www.voanews.com/a/what-is-behind-the-violence-in-ethiopia-s-other-conflict-
Sudan Tribune
- ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የሚዋሰኑ አካባቢ ላይ ያሉ የእርዳታ ድርጅቶችን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ነው የጻፈው
የተነሱ ነጥቦች
- ሱዳን የኢትዮጵያን የእርዳታ ድርጅቶችን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟንና የተፈጠረው ግጭት መባባሱን ተከትሎ ለደህንነታቸው ስላደረባቸው ይህ መወሰናቸው
- የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መቀበያ ማዕከልን ለቀው እንዲወጡ ማሳሳባቸው
- በመንግስት እና በህወሓት ሀይሎች መካካል በተፈጠረው ግጭት የትግራይ ክልል ሰዎች ወደዛ ተሰደው እንደነበር
- አሁን ላይ ግን በመንግስት እና በህወሓት መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት በኤርትራ ሀይል በሚደገፈው መንግስት ህወሓት እንደተበደለ መገለጹ
- በዲማ እና ቁዲማ አካባቢዎች በሱዳን-ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የድንበር ትሪያንግል አቅራቢያ በሁለቱ ወገኖች መካከል ከፍተኛ ወታደራዊ ግጭት መቀጠሉን የመረጃ ምንጮች ለሱዳን ትሪቡን ማረጋገጣቸው
- በተጨማሪ የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ እንደገለፀው የውጭ ድርጅቶች በዲማ ዙሪያ ወታደራዊ ግጭቶች ከተጠናከሩ በኋላ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዛቸው የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
ሊንክ https://sudantribune.com/article263629/
- በተጨማሪ ሱዳን ከ200 በላይ የኢትዮጵያ የቀድሞ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ጥገኝነት መስጠቷንም የሚገልጽ ጽሁፍም ወቷል።
የተንሱ ነጥቦች
- የሱዳን መንግስት በአወዛጋቢው የአቢዬ ክልል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ ውስጥ ላገለገሉ 247 ጥገኝነት መስጠቱኝ
- በጦርነቱ ምክንያት ከትግራይ ክልል የመጡት 649 የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይሎች በአሁኑ ወቅት በሱዳን ኡም ቀርኩር ካምፕ ከተጠለሉት መካከል እንደሚገኙ ።
- የሱዳን የገዳረፍ ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ዕለታዊ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከ649 ስደተኞች መካከል 247ቱ የስደተኞች መብት እንደተሰጣቸው ።
- ከእርዳታው በፊት ባለስልጣናት ለጥገኝነት ጠያቂዎቹ የስደተኛ ሁኔታ ውሳኔን ያደርጉ ነበር ሲል ኦፊሴላዊው የዜና ወኪል መናገሩን ።
- እነዚህ የተመድ ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ባለፈው በተነሳው ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገር ቤት መመለስ እንደማይፈልጉ እና ከተመለሱም ለደህንነታቸው ስጋት እንደሚፈሩ ።
- በአሽባሪው ህወሓት እና በመንግስት ሃይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት በመላ ሀገሪቱ የጅምላ እስራት እንደተፈፀመባቸው የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
ሊንክ https://sudantribune.com/article263622