የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ሐምሌ 18፣ | 2014 ዓ.ም – July 25 |2022
Sudan Tribune
- የአሜሪካው ልኡካን ስለትግራይ የሰላም ድርድር ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸውን የሚዘግብ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በህወሓትና የፌደራል መንግስት ሰላማዊ ድርድሩ ጉዳይ ላይ ለመምከር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው
- “ልዩ መልዕክተኛው ከጁላይ 24 እስከ ነሀሴ 1 ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ግብፅ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ኢትዮጵያ እየተጓዙ ነው” ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቅዳሜ መናገሩን ።
- በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ያደረገው ጉዞ ከ ህወሐት ጋር ያለውን ግጭት ለማስቆም መንግስትን ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለማምጣት አሜሪካ ግፊት ማድገር እንደምትፈልግ ።
- ልዩ መልዕክተኛ ሀመር ኢትዮጵያ ውስጥ በነበሩበት ወቅት በትግራይ ግጭት የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የመብት ጥሰቶች የሰብአዊ ርዳታ አሰጣጥ እና ተጠያቂነት ላይ ያለውን ሂደት ለመገምገም አሜሪካ ለመገምገም እድል እንደምታገኝ
- አሜሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ሰዎች ሁሉ ዘላቂ ሰላም፣ ደህንነት እና ብልጽግና ለማምጣት የሚካሄደውን ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት ለመደገፍ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ማራመድ እንደቀጠለች ልዑኩ መናግሩን
ሊንክ https://sudantribune.com/article261813/
Horseed Media
- የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ ካቋረጡ በኋላ ግብፅን ጎበኙ የሚል መልክት ያለው ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሚስተር ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና የልኡካን ቡድኑ ትናንት እሁድ ካይሮ ግብጽ መግባታቸውን ።
- የሶማሊያው ፕሬዚደንት ከግብጹ ፕሬዚደንት ጋር በሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙርያ ምክክር እንዳደረጉ
- የፕሬዚዳንቱ የልዑካን ቡድን በግብፅ ውስጥ ካሉ ፖለቲከኞች እና ባለስልጣናት ጋር ጥልቅ ግንኙነት ያለው የብሔራዊ መረጃ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ማሃድ ሞሃመድ ሳላድ እንደተገናኙ
- ይህ የግብፅ ጉዞ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ወደ ኢትዮጵያ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ ከተሰረዘ ከጥቂት ቀናት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዞው እንዲራዘምለት ጠይቆ እንደነበር።