Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ሐምሌ 16፣ | 2014 ዓ.ም – July 23 |2022

Reuters

  • የሶማሊያ አልሸባብ ቡድን በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ጥቃቶችን  እንደፈጸመ የሚዘግብ ነው ።

በዘገባው  የተነሱ  ነጥቦች

  • የሶማሊያ እስላማዊ ቡድን አልሸባብ ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ ሁለት መንደሮች ላይ ጥቃት በማድረስ 17 ሰዎች በሶማሌ ክልል ውስጥ ሶስት ሲቪሎች እና የኢትዮጵያ ፖሊሶች ሲገደሉ 63 ተዋጊዎቹ መገደላቸውን በስፍራው የሚገኘው የኢትዮጵያ የጸጥታ አዛዥ መናገራቸው
  • በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች በአልሸባብ የሚሰነዘረው ጥቃት አዲስ የተለመደ እንድሆነና በአከባቢው እና በሶማሊያ ውስጥ ጠንካራ የኢትዮጵያ የጸጥታ ጥበቃ እና የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሃይል አካል በመሆናቸው
  • የኢትዮጵያ ኮማንደር በመጀመሪያ የሟቾችን ቁጥር 17 የኢትዮጵያ ፖሊሶች መገደላቸውን ቢገልጽም ከሟቾቹ መካከል ሲቪሎች እንደሚገኙበትም  ማሳወቃቸው   ዋና ዋና የዘገባው ነጥቦች ናቸው።

ሊንክ   https://www.reuters.com/world/africa/somalias-al-shabaab-group-rare-attack-near-ethiopia-border-2022-07-21/

Middle East Monitor

  • ሶማሊያ ወታደሮቹ በኢትዮጵያ የትግራይ ግጭት ውስጥ እጃቸው እንዳሌለበት ማሳወቋን የሚተነትን ነው።

በዘገባው  የተነሱ  ነጥቦች

  • የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ቃል አቀባይ በኤርትራ የሰለጠኑ የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያ የትግራይ ግጭት ውስጥ እንዳልተሳተፉ የሚገልጹ ዘገባዎች ሀሰተኛ እንደሆኑ መግለጻቸው።
  • በተሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አብዲካሪን አሊ ካር 5,000 “የጠፉ” የሶማሊያ ሰልጣኞች መገኘታቸውን እና መንግስት ወደ ሶማሊያ ለመመለስ የሀገሪቱ መንግስት እየሰራ መሆኑ
  • በ2021 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ በኤርትራ የሰለጠኑ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ወታደሮች ጋር በመሆን የኤርትራን ድንበር አቋርጠው በትግራይ ግጭት ውስጥ መሳተፋቸውን መግለጻቸውን ማስታወሱ  ዋና ዋና ከዘገባው ነጥቦች መካከል ናቸው።

ሊንክ   https://www.middleeastmonitor.com/20220721-somalia-denies-troops-involvement-in-ethiopia-tigray-conflict/

VOA

  • የሶማሊያው አልሸባብ ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድንበር ዘለል ጥቃት መጀመራቸውን ነው የሚዘግብው። 

በዘገባው የተነሱ ዘገባወች

  • የሶማሊያው አልሸባብ ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድንበር ዘለል ጥቃት በመሰንዘር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና ሊዩ ፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውንና ቁጥራቸው በውል የማይታወቁት ላይ ጉዳት መድረሱ  ።
  •  አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ሲሰነዝር ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ እንደሚታመን
  • የሶማሊያ ወታደራዊ ምንጮች እና የሊዩ ፖሊስ ባለስልጣን ለቪኦኤ እንደተናገሩት በብዛት የሚቆጠሩ የአልሸባብ ተዋጊዎች ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሐሙስ እረፋድ  ላይ  መግባተቸው
  • የሶማሊያ ባለሥልጣን በአልሸባብ ላይ የደረሰውን ጉዳት ቁጥሩን ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑም ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነው በኩል የሚገኘው የሶማሊያ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በግጭቱ ቢያንስ 87 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ለቪኦኤ  መናገራቸው
  • እስላማዊው ታጣቂ ቡድኑ ለምን ጥቃቱን እንደጀመረ ግልጽ  እንዳልሆነ እና ነገር ግን የጸጥታ ሀይሎች ቡድኑ አሁንም አደገኛ መሆኑን ለማሳየት እየሞከረ ሊሆን እንደሚችል እና የኢትዮጵያ መከላከያ ከህወሐት ጋር በነበረው ግጭት እንደተዳከመ በማሰቡ እንደሆነ እንደገመቱ

ሊንክ    https://www.voanews.com/a/somalia-s-al-shabab-militants-launch-attack-in-ethiopia-heavy-casualties-reported/6669872.html

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *