Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

8  Aug 14 , 2023

  Reuters

  • በኢትዮጵያ አማራ ክልል በየአየር ጥቃት ምክንያት የ26 ሰዎች ህይወት እንዳለፈ እንደሚጠረጠር የሚገልጽ ነው።

  የተነሱ ነጥቦች

  • በኢትዮጵያ አማራ ክልል በሳምንቱ መጨረሻ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ቢያንስ 26 ሰዎች መሞታቸውን የሆስፒታሉ ባለስልጣን ሰኞ እንደገለጹ እና በመንግስት የተቋቋመው የመብት ተሟጋች ተቋም በዚህ ወር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በሰላማዊ ዜጎች ላይ መጠነ ሰፊ ግድያ መፈጸሙን እንደገለጸ
  • የፌደራል ሃይሎች ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ የፋኖ ታጣቂዎችን ከአማራ ዋና ዋና ከተሞች መስወጣታቸውን ቢገልጹም በክልሉ ሌሎች አካባቢዎች ግጭቶች መቀጣላቸውን ይኸው ተቋም መገለጹ
  • የፌደራል መንግስት የአማራን ክልል ለማዳከም እየሞከረ ነው በሚል የፋኖ ውንጀላ የተቀሰቀሰው ይህ ጦርነት የሰሜኑ ጦርነት ካበቃ በኋላ በኢትዮጵያን የገጠማት ትልቁ የጸጥታ ችግር እንደሆነ
  • የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ጦርነት ወቅት የፌደራል ሃይሎችን ሲደግፍ የነበረው ፋኖ ኢ-መደበኛ ሚሊሻ ያቀረበውን ውንጀላ እንዳስተባበለ
  • በክልሉ የስራ ማቆም አድማው ትናንት እሁድ በፍኖተ ሰላም ከተማ መደረጉ በነዋሪዎች እንደተገለጸ
  • የኢሰመጉ መግለጫ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ክስተቶችን መርማሪዎቹ እንደመዘገበ እና ከነዚህም መካከል መንገድ የዘጉ ሰላማዊ ሰልፈኞች መገደላቸውን፣ ከፖሊስ ጣቢያዎችና ማረሚያ ቤቶች የተዘረፉ የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች፣ በአማራ ክልል አስተዳደር ባለስልጣናት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ጨምሮ መመዝገቡን እንደገለጸ
  • በአማራ ዋና ከተማ ባህር ዳር ሰላማዊ ሰዎች በመንገድ ላይ ወይም ከቤታቸው ውጭ ተገድለዋል ያለው ኢሰመጉ በክልሉ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ በሆነችው ጎንደር ብዙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን እና በሸዋ በጸጥታ ሃይሎች ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ መፈጸሙን የሚገልጹ ታማኝ ማስረጃዎች መኖራቸውን ተቋሙ እንደገለጸም የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።

ሊንክhttps://www.reuters.com/world/africa/suspected-air-strike-kills-26-ethiopias-amhara-reg

 Africa news

  • በኢትዮጵያ ፖሊስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቶዎች የሚቆጠሩ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ የሚተነትን ነው።

   የተነሱ ነጥቦች

  • ፋኖ በመባል የሚታወቁት የአካባቢ ሚሊሻ ታጣቂዎች በርካታ ዋና ዋና ከተሞችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ያን ለመቀልበስ የኢትዮጵያ መንግስት ካቢኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን
  • የኢትዮጵያ የፓርላማ ባለስልጣናት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ ፍተሻ ለማድረግ እና የሰዓት እላፊ ገደቦችን የሚጥሉ ድንገተኛ እርምጃዎችን መደበኛ ፈቃድ ለመስጠት ሰኞ ድምጽ እንደሚሰጡ
  • በዚህ ጊዜ “የአማራ ተወላጆች በብዛት እየታሰሩ ነው” ሲል ኢሰመጉ የፌደራል መንግስት እስሩን እንዲያቆም መጠየቁ
  • በጅምላ እስሩ የአማራ ተወላጆች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን አክቲቪስቶችም እየገለጹ መሆናቸው
  • በጅምላ እስራቱ ጠበቆች እና ጋዜጠኞች ጭምር እየታሰሩ እንደሆነ የሚገልጹት ዋና ዋና ነጦቦቹ ናቸው።

ሊንክ     –  https://www.africanews.com/2023/08/14/ethiopian-police-arrest-hundreds-during-state-of-e

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *