Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ታኅሳሥ 21፣ | 2015 ዓ.ም – Dec 30 | 2022

Africa news

 • የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወደ ትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ ማሰማራቱን የሚገልፅ ጽሁፍ ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊሶች ባለፈው ሀሙስ ወደ ትግራይ መቀሌ መሰማራት የጀመሩ ሲሆን ይህም ለሁለት ወራት ያህል በቆየው የሰላም ስምምነት አዲስ ደረጃ ላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
 • በህዳር 2020 በፌደራል መንግስት እና በህወሓት ታጣቂዎች መካከል ጦርነት  መጀመሩን ።
 • ህወሓት የሰራዊቱን ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ መንግስት ወታደሮቹን ወደ ሰሜኑ ክልል  ትግራይ መላሁን ።
 • የአሜሪካ ዘገባ እንደሚያሳየው በግጭቱ እስከ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች  መሞታቸውን ።
 • ህዳር 2 በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ የተደረሰው ስምምነት የህወሓት ሃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት በትግራይ የፌደራል ባለስልጣን እንደገና እንዲቋቋም እና የክልሉን ተደራሽነት ለማሳያት የሚያስችል ነው ።
 • በታህሳስ 22 ሁለቱ ወገኖች የሰላም ስምምነቱን አፈፃፀም ለመከታተል የጋራ ክትትል እና ተገዢነት ዘዴ ለመፍጠር  መስማማታቸውን ።

ሊንክ    https://www.africanews.com/2022/12/29/ethiopias-federal-police-deploys-to-t

Reuters

 • የኢትዮጵያን እና የህወሓት ባለስልጣናትን የእርቅ ስምምነት ለማጠናከር ሸምጋዮች  መሰብሰባቸውን የሚናገር ዘገባ ነው ።

የተነሱነጥቦች

 • የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ከዚህ በፊት በነበረው ጥላቻን ወደ ጎን በመተው አሁን ላይ እየታየ ያለው የስምምነት አካሄድ ለሁለቱም ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ ማድረጉን ።
 • ህዳር 2 የተኩስ አቁም ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን የገደለ እና ሚሊዮኖችን ያፈናቀለውን የሁለት አመት ግጭት ጸጥ ማድረጉን ነገር ግን የስምምነቱ ክፍሎች ተግባራዊነት ከተጠበቀው በላይ  መዘግየቱን ነው ።
 • በትግራይ የሚገኙ የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች እንደሚሉት ከኤርትራ ጎረቤት የነበሩ ወታደሮች በስምምነቱ  ውል መሰረት ለቀው መውጣት እንደነበረባቸው ።
 • በተጨማሪም አሁንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በረሃብ እና እርዳታ በሚፈልጉበት ክልል በሚገኙ በርካታ ከተሞች  እንደሚገኙ ።
 • የኤርትራ መንግስት የሰጠው አስተያየት አለመኖሩን የኤርትራ ሃይሎች ጉዳይም ሆነ ወደ ትግራይ የሚሰጠው አገልግሎት ወደ ነበረበት መመለስ እና ሰብአዊ እርዳታ በአስታራቂዎች የሚቋቋመው የክትትል ቡድን አጀንዳ ይሆናል ተብሎ  እንደሚጠበቅ ።
 • ሸምጋዮቹ በትግራይ ርዕሰ መዲና መቀሌ እየተሰባሰቡ ነበር ሲሉ የክልሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ ቃል አቀባይ ኑር መሀሙድ ሼክ ሃሙስ እለት መናገራቸውን ።
 • የሕወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታችውን ።
 • በሰላሙ ስምምነቱ መሰረት የክትትል ቡድኑ እስከ ህዳር 22 ድረስ ይቋቋማል ተብሎ  እንደነበረ ነገር ግን የትግራይ መሪዎች ስለ እርቅ ማቋረጡ እና ሌሎች የውል ድንጋጌዎችን በመተግበሩ ቅሬታ ማቅረባችውን ።
 • በሌላ በኩል ወደ ተሻለ ግንኙነት የሚመራበት ፍጥነት እየጨመረ የመጣ ይመስላል በትላንትናው እለት የመንግስት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ከጀመረ ከ18 ወራት በኋላ በረራውን  መቀጠሉን እና ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን ወደ መቀሌ እና ሌሎች 27 ከተሞች ያገናኘ ሲሆን መንግስት ሰብአዊ እርዳታ እየተጠናከረ ነው ።

ሊንክ     https://www.reuters.com/world/africa/mediators-meet-bolster-ethiopia-truce-amid-signs

Abc news

 • የኢትዮጵያ ፖሊስ ወደ ትግራይ ዋና ከተማ የገባው በሰላም ስምምነቱ ምክንያት እንደሆነ  የሚገልጽ ዘገባ ነው።

የተነሱነጥቦች

 • የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባለፈው ወር በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት አመራሮች መካከል በተደረገው የሰላም ስምምነት መሰረት አባላቱ ከአንድ አመት በላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌ መግባታቸውን ማስታወቁን ።
 • የሰላም ስምምነቱ በህዳር 2020 በፌዴራል እና በክልል ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት  አሁን ያለውን የሰላም ስምምነቱ ምንጭ መሆኑን
 • እንደ ዩኤስ ግምት ከሆነ በመንግስት እና በህወሓት መካከል በነበረው ግጭት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን  ማፈናቀሉን ።
 • የፌደራል ፖሊስ በመቀሌ የሚገኙ መኮንኖች በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት የፌደራል ፖሊስ የሚሰጠው ድጋፍ የአየር ማረፊያዎችን የሃይል እና የቴሌኮም ተቋማትን እና ባንኮችን እንዲጠበቁ የማድርግ ስራ እንደሚሰራ የፌደራል ፖሊስ በፌስቡክ ገፁ ላይ ማስቀመጡን ።
 • በሰሜን ትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎቶች እና የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦቶች ቀስ በቀስ እንደጀመሩ ነው።
 • ሐሙስ እለት አዲርቃይ፣ እንቺኮ፣ ማይ ፀብሪ እና ራማ ከተሞች ከአንድ አመት ተኩል በላይ ከአውታረ መረቡ ጋር  መገናኘታቸውን ።
 • በትናንትናው እለት ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድም በሽሬ ከተማ አገልግሎቱን መጀመሩን እና ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ በከፍተኛ ፍላጎት ማደጉን  ነው ።

ሊንክ   https://abcnews.go.com/International/wireStory/ethiopian-police-enter-tigray-capita

Reuters

 • የኤርትራ ወታደሮች የሰሜን ኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞችን ለቀው  መውጣታቸውን የአይን  ምስክሮች መናገራቸውን የሚተነትን ጹሁፍ ነው ።

የተነሱነጥቦች

 • በሰሜን ትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት የኢትዮጵያን ፌዴራላዊ መንግስት በመደገፍ የተዋጉት የኤርትራ ወታደሮች ከሽሬ እና አክሱም ዋና ዋና ከተሞችን ለቀው ወደ ድንበር ማቅናታቸውን እማኞች ለሮይተርስ  መናገራቸውን ።
 • የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣት የጀመሩት በመንግስት እና በህወሓት መካከል በተደረገው ስምምነት መሰረት መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ ነው ።
 • በተጨማሪ  በህወሓት እና በመንግስት መካከል የተደረገው ስምምነት አንዱ እና ዋናኛው የኤርትራ ወታደሮች ከ ትግራይ መውጣት እንዳለባቸው ነው ።

ሊንክ    https://www.reuters.com/world/africa/eritrean-soldiers-pull-out-major-tigray-towns

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *