Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ

ጥር 21፣ 2017 ዓ.ም Jan 29 2025

middleeasteye

የቱርክ ገዥው የፍትህ እና ልማት ፓርቲ (ኤኬፒ) ከሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለማጠናከር በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሁለት ስምምነቶችን እየተፈራረሙ እንደሆነ አንስትዋል።

ዋና ዋና ነጥቦች

  • የኤኬፒ ምክትል ሊቀመንበር ዛፈር ሲራካያ ከሶማሊያ ሰላምና ልማት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አብዱራህማን መሀመድ ሁሴን ጋር በአንካራ የሁለትዮሽ ትብብር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን በማንሳት በመጪው አርብ ከኢትዮጵያ ገዥው የብልጽግና ፓርቲ (PP) ጋር ተመሳሳይ ስምምነት በአዲስ አበባ ይፈራረማል።
  •  ስምምነቱ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የጋራ ምርምር፣ ስልጠና፣ ምክክር እና የመረጃ ልውውጥን ለማመቻቸት ያለመ እንደሆነ በማንሳት ቱርክ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ገለልተኝነቱን ጠብቃ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ውጥረት ለመፍታት በድርድር ላይ እንደ ሸምጋይ ሆናለች።
  • ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በታህሳስ ወር በአንካራ የመግባቢያ ሰነድ የሶማሊያን የግዛት አንድነት የሚያረጋግጥ እና ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባህር ዳርቻ በኩል እንድትጠቀም የሚያስችል ውይይት ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውን አንስትዋል።
  • ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ “የክልላዊ አመለካከት” ያላት ሲሆን በአካባቢው ካሉ ሌሎች ሀገራት ጋር ግንኙነት ለመፍጠር እየሰራች ነው።
    • ሊንክ  https://www.middleeasteye.net/news/turkey-deepens-ties-somalia-and-ethiopia-through-political-deals
Newscentral.africa

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፍትሃዊ፣ሰላማዊ እና ሁሉንም ያሳተፈ ማህበረሰብ ለመገንባት በማለም የመጀመርያውን የሰብአዊነት ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ አስመረቀ።
 ዋና ዋና ነጥቦች
  • የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጥር 27 ቀን 2025 የመጀመሪያውን ግብረ ሰናይ ትምህርት ቤት እንዳስመረቀ በማንሳት  ትምህርት ቤት ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ እና ሁሉንም ያካተተ ማህበረሰብን ማፍራት ነው።
  • ትምህርት ቤቱን ለትግራይ ጦርነት ሰለባዎች መታሰቢያ እንደሆነ ፕሬዝዳንት አበራ ቶላ መግል፡አጻቸውን።
  • ውጥኑ የወደፊት ትውልዶች ሰብአዊነትን እንዲጠብቁ እና የግለሰብን ክብር እንዲያከብሩ ለማስተማር ያለመ ነው።
  • በአዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ አካባቢ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ የአንድ አመት የዲፕሎማ ፕሮግራም ከዘጠኝ ኮርስ ሞጁሎች ጋር እንደሚሰጥ አንስትዋል።
    • ሊንክ https://newscentral.africa/ethiopia-opens-first-humanitarian-school-in-addis-ababa/
Biometricupdate

በ2022 ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከሁሉም የህዝብ አገልግሎቶች ማለት ይቻላል ጋር ይገናኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ዋና ዋና ነጥቦች

  • እ.ኤ.አ. በ2022 ስራ የጀመረው ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ሁሉም የህዝብ አገልግሎቶች ጋር ሊገናኝ እንደሚችል  ተብሎ እንደሚጠበቅ መታወቂያው ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ለት/ቤት ምዝገባ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ማለትም የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ እና ትምህርት ቤቶች ትብብር ነው።
  • እርምጃው ከ116ቱ የአስተዳደር ክፍል (ወረዳዎች) ውስጥ 21ዱ ቀድሞውንም ዲጂታይዝ በማድረግ ሁሉንም አገልግሎቶች ዲጂታል ለማድረግ የተያዘው ሰፊ እቅድ አካል እንደሆነ በማንሳት የፋይዳ መታወቂያ ከብዙ የመንግስት እና የግሉ ሴክተር አገልግሎቶች፣ ከስደተኛ፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎቶች ጋር ተዋህዷል።
  • መታወቂያው ለፐብሊክ ሰርቫንት ፣የታክስ ስርዓቱ ፣የመንግስት ግዥዎች ፣የሀገር ውስጥ በረራ ማመቻቸት እና የባንክ ግብይቶች የግዴታ እንዲሆን ተደርጓል።
  • በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ወሰን ውስጥ የተቀናጁ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለማቃለል ኤንዲፒ ከአራት የመንግስት ኤጀንሲዎች ጋር መተባበር ማድረጉን በማንሳት  በ11.4 ሚሊዮን ሰዎች የተገኘው የፋይዳ መታወቂያ፣ የዲጂታል ቅልጥፍናን ለማሳደግ እና የበለጠ አስተማማኝ ሀገር አቀፍ የመለየት ሂደትን ለማረጋገጥ የተነደፈ ነው።
  • አገሪቱ በ2030 ከቁልፍ የገንዘብ ድጋፍና የቴክኖሎጂ አጋሮቿ ጋር በመሆን የፋይዳ መታወቂያ ለ90 ሚሊዮን ሰዎች ለመስጠት አቅዳለች።
    • ሊንክ https://www.biometricupdate.com/202501/school-registration-adds-up-to-expanding-use-cases-of-ethiopias-digital-id

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *