Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌስቡክ ገጽ ከፍተኛ ተሳትፎ ከሚያሳዩ የአለም መሪዎች ገፆች አንዱ ነው::

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፌስቡክ ገጽ ከፍተኛ ተሳትፎ (Engagement) እና መስተጋብር (Interaction) ከሚያሳዩ የአለም መሪዎች ገጽ አንዱ እንደሆነ ተገለፀ። ፌስቡክን ከሚጠቀሙ የሀገራት መሪዎች ውስጥ በተለየ ሁኔታ ገጻቸው በተሳታፊዎች Interaction (መስተጋብር) መጠን ሲለካ ከፍተኛ የሆነው አፍሪካዊው መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደሆኑ ትዊፕሎማሲ የሚባለው ታዋቂ አወዳዳሪ ድረገጽ አስታወቀ።

በአፍሪካ ካሉ መሪዎች ውስጥ በአንደኝነት የተቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሲሆኑ ሃመድ ባካዮኮ ከኮትዲቯር፣ አብዱልፈታ አልሲሲ ከግብጽ፣ ናንአኩፎ አዶ ከጋና እና ዩዌሪ ሙሴቪኒ ከዩጋንዳ እስከ አምስተኛ ያሉ ደረጃዎችን ይዘዋል። በሌላም በኩል የፌስቡክ ገፅ በየጊዜው በሚያወጣው የፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎች ዝርዝር ደረጃ መሠረት ከአፍሪካ መሪዎች በሳምንት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛተሳትፎ (Engagement) የታየበት የፌስቡክ ገጽ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሊ የፌስ ቡክ ገፅ እንደሆነም አሳይቷል።

በዚህ የተሳትፎ (Engagment) ንጽጽር በሰፊ ልዩነት በ1.1 ሚሊዮን ከአናት የተቀመጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፌስቡክ ገጽ ከሁሉም መሪዎች በልዩ ሁኔታ የተለያዩ የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ሃሳቦች እና ተግባራት በወቅቱ ለህዝብ ግልፅ በማድረጉ፣ በወቅታዊ መልዕክቶች ታጅቦ በመቅረቡ፣ በሚያማምሩ እና ተስፋን በሚጭሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ክንውኖችን በማቅረቡ እንደሆነ የተለያዩ ድረገፆች እየገለፁ ይገኛሉ። የጠቅላይ ሚኒስትር ፌስቡክ ገፅ አሁን ከ3.7 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው ሲሆን፤ በተለያየ መልኩ ህዝብን ከመሪ የማገናኛ ቁልፍ የተግባቦት ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስ ቡክ ገፅ የተለያዩ መረጃዎችን በአማርኛ ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በማቅረብ ከአንድ አመት ተኩል በላይ አስቆጥሯል።

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *