Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ኢትዮጵያ መጥተዋል

የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ኢትዮጵያ መጥተዋል

የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ኢትዮጵያ መጥተዋል

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈችውን ውሳኔ የተቃወሙት ሴናተር ጂም ኢንሆፌ አዲስ አበባ ገቡ::አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ያሳለፈችውን የቪዛ እንዲሁም በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የኢኮኖሚ እና የፀጥታ ዘርፍ ድጋፍ ተቃውመው የተከራከሩት የዩኤስ አሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፌ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሴናተሩን የተቀበሉት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ “የኢትዮጵያውያን ወዳጅ የሆኑትን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር፣ ጂም ኢንሆፌን ወደ ሁለተኛው ቤትዎ- እንኳን ደኅና መጡ እላለሁ” ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ሴናተር፣ ጂም ኢንሆፍ  ባለፈው ሳምንት አሜሪካ  በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈችውን  የቪዛ እገዳ አስመልከተው “የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን የቪዛ እገዳዎችን እቃወማለሁ” ማለታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስትን ከሽብርተኛው ድርጅት ሕውሓት ጋር በተመሳሳይ ረድፍ ለማስቀመጥ መሞከር ተቀባይነት የለውም በማለት፤ “የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ሰላማዊ መፍትሔዎችን ለማምጣት እየሰራ ይገኛል፤ ሰላምንና አንድነትን ከማምጣት ውጪ ሌላ አካሄድ አልሄደም”  በማለትም ውሳኔውን በመቃወም  ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ገልጸው ነበር።

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *