የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ታኅሳሥ 13፣ | 2015 ዓ.ም – Dec 22 | 2022
VOA
- ኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ተወካዮችና የህወሓት አመራሮች የሰላም ድርድሩን ተግባራዊነት ለመገምገም እንደተገናኙ የሚገልጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የህወሓት አመራሮች የሰላም ስምምነት ቀጣይ እርምጃዎች ላይ ለመወያየት በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ እየተገናኙ እንደሆነ
- የግንኙነቱ ዓላማ በደቡብ አፍሪካ በህዳር ወር የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ዙርያ እንደሆነ
- የረቡዕ ስብሰባ ህወሀት በትግራይ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የሚፈለጉትን ሰብአዊ እርዳታዎችን ለማግኘት እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናግረው እንደነበር
- በጦርነቱ ወቅት ወደ ትግራይ የገቡት የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን መንግስት ለመደገፍ ወደ ትግራይ በገቡበት ወቅትም ሆነ አሁንም ለችግሮቹ ተጠያቂ እንደሆነ ህወሓት እየከሰሠ እንደሆነ
- የኤርትራ ሃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃቶ እያደረሰኡ እንደሆነና በችግርቹ ለተሰቃየው ህዝብ የገባዉን ዕርዳታ እየዘረፉ እንደሆነ በመግለጽ መንግስት እንዲያስቆም ህወሓት በትግራይ ክልል ሚዲያዎች መግለጻቸው የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
ሊንክ – https://www.voanews.com/a/ethiopia-tigray-rebel-officials-meet-to-review-implementatio
Chimp Report
- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የአፍሪካ ሀገራትን የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይን እንዲቀበሉ ጥሪ አቀረቡ እንደሆነ የሚገልጽ ነው
የተነሱ ነጥቦች
- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተለይ አካባቢን በመጠበቅ በአረንጓዴው ሌጋሲ ፕሮጀክት ላስመዘገቡት የላቀ አፈፃፀም በአሜሪካ የስኬት አካዳሚ እና በግሎባል ተስፋ ጥምረት የአፍሪካ መሪነት ሽልማት እንደ ተበረከተላቸው
- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሰጡት የአቀባበል መግለጫ ላይ አፍሪካ በብዙ የስኬት ታሪኮች ተሞልታ ያለፈች እንደሆነች መግለጻቸው
- የአፍሪካ አገሮች የችግር ፈጣሪዎች ናቸው በሚለው አመለካከት ሁልጊዜ የውጭ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የሚነገረው ጊዜ ያለፈበት አጀንዳ እንደሆነ መጥቀሳቸውን የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
ሊንክ – https://chimpreports.com/ethiopian-pm-rallies-african-countries-to-embrace-environm