Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ታኅሳሥ 8፣ | 2015 ዓ.ም – Dec 17 | 2022

NPR

  • የፌስቡክ የጥላቻ ይዝቶችና ብጥብጥና ጦርነት የሚያባብሱ መረጃዎች ሲሠራጩ እርምጃ ባለመውሰዱ በኢትዮጵያ ውስጥ ብጥብጥ እንዲፈጠር አድርጓል በሚል ክሥ እንደቀረበበት ነው የጻፈው።

የተነሱ ነጥቦች

  • ፌስቡክ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የጥላቻ እና አደገኛ ይዘቶችን በማስቀደም የጎሳ ግጭቶችን ሲያቀጣጥል የማስተካከያ እርምጃ ባላመውሰዱ ሜታ ክሥ እንደቀረበበት።
  • በዚህ ሳምንት በኬንያ ናይሮቢ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበው የሕግ ክስ ጀርባ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች እና አንድ የኬንያ የሕገ መንግሥት መብት ተሟጋች ቡድን እንዳሉ
  • ፌስቡክ ከሌላው ዓለም የአፍሪካብ ተጠቃሚዎቹን በተለየ መልኩ እንደሚመለከት በዝያም የጥላቻ ይዘቶች ሲሰራጩ ችላ በማለት ብዙ እልቂት እንዲፈጠ ማድረጉ።
  • የሜታ ኩባንያ ቃላቀባይ ፌስቡክ ይዘቶችን ፈትሾ የማሳለፍ ሥራ ላይ እጅግ ብዙ ገንዘብ እንዳወጣበት
  • አንዳንድ ይዘቶችን ለመለየት የቋንቋን ውስንነቶች እንደያዙት የሚሉት ከነጥቦቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ሊንክ    https://www.npr.org/2022/12/17/1142873282/facebook-meta-lawsuit-ethiopia-

Plenglish

  • ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ ጸረ በሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ላይ ያላቸውን ትብብር እንደሚጠናክሩ የሚያብራራ ማስማማታቸውን ነው።

የተነሱነጥቦች

  • የሁለቱም ሀገራት ቁርጠኝነት ይፋ የሆነው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ፋሃድ ኦባዳላህ አልሁመዳኒ አልሞታይሪ ባደረጉት ውይይት እንደሆነ
  • ገብረሚካኤል እና አልሁማዳኒ አልሞታይሪ የሁለትዮሽ ትብብርን ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስወገድ ተባብሮ መስራት እንደሚያስፈልግ መስማማታቸው።
  • ዲፕሎማት ጄኔራሉን የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ትብብር ድርጅት (ኢጋኮ) ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው ታህሳስ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የክልሉ አካል 24ኛ ጉባኤ ላይ የእንኳን ደስ አላችሁ ማለታቸው የሚሉት በጽሁፉ ከተነሱት ዋና ዋና ሀሳቦች ናቸው።

ሊንክ    – https://www.plenglish.com/news/2022/12/16/ethiopia-and-saudi-arabia-to-expand-co

TFI Global News

  •  አብይ አህመድ ሌላ መሪ ባላደረገው መልኩ ባይደንንና ግብረ አበሮቹን አሸንፏቸዋል የሚል ነው።

የተነሱነጥቦች

  • በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከኢትዮጵያ የበለጠ ቢደንን ያስደነቀ ህዝብ እንደሌለ
  • የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአፍሪካ አህጉር የአሜሪካናን ጣልቃ ገብነት ተቀናቃኝ እንደሆኑና አሜሪካ በአፍሪካ ላይ የምታደርገውን ጫና ትርክቶችን በማሸነፍ አስደናቂ አቋም እንዳሳዩ
  • በቅርቡ በተካሄደው የአፍሪካ-አሜሪካ ስብሰባ፣ አብይ አህመድ ባይደንን እና ግብረ አበሮቻቸውን ሙሉ በሙሉ በመርታት አሜሪካ እንዳሳፈሯት
  • የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጉባኤው ዋሽንግተን ዲሲ ሲያርፉ ባይደን ወደ ዶ/ር ዐብይ እንዳይጠጉ በጥበቃ ተይዘው እንደንበር
  • ብሊንከን በዋሽንግተን ዲሲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር እየተገናኘ ሳለ፣ በዋሽንግተን በሚገኘው የስብሰባ ማእከል ውጭ የትግራይ ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ተዘጋጅተው እንደነበርና በተወሰነ መልኩም ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐብይ መጋበዝ እንደሌለባቸው ደም በእጃቸው ላይ አለ በሚል የክሥ ድምጽ ማሰማታቸው የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።

ሊንክ   https://tfiglobalnews.com/2022/12/17/abiy-ahmed-has-destroyed-biden-and-his-accomplices-

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *