Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

Al monitor  

  • ግብጽ አዲስ የናይል ሳት ሳታላይትን ከአሜሪካ የሳታላይት ማምረቻና ማምጠቅያ ማዕከል ማምጠቋንና በሥራውም ከአፍሪካ ጋር በትሥሥር ለመስራት እንደምትፈልግ መግለጿን ነው የሚተነትነው።
  • አዲሱ ሳተላይት የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን፣ አዳዲስ የነዳጅ ቦታዎችን በምስራቃዊ ሜዲትራኒያን ጫምሮ ከግብጽ ግብፅ ሩቅ አካባቢዎች ያተኮረ የኢነትርኔት ሽፋን ለመስጠት የሚል ቢዘገብም አካባቢውን በተለየ መልኩ በመረጃ መረብ ቁጥጥር ለማድረግ ያለመ የሚመስል እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ ነው።
  • ዘገባው ግብጽ በግድቡ ዝርያ አስገዳጅ ስምምነት እንዲፈጸን የምትፈልግ ቢሆንም ኢትዮጵያ ኝ ያለምንም ስምምነት ግድቡን ለመሙላት እንደምትፈልግ ለማሳየት የፈለገ ዘገባ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ   https://www.al-monitor.com/originals/2022/06/egypt-promotes-ties-africa-new-satellite

The paradise

  • በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና እና ህወሓት በትግራይ ክልል የመብራት እና የባንክ አገልግሎትን ወደ ነበረበት ለመመለስ ሚስጥራዊ ስምምነት ደረሱ ይላል።
  • ስምምነቱ የተደረሰው በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ አስተባባሪነት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፅህፈት ቤት እና የሕወሃት መሪ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል መካከል እንደተደረገ በመግለጽ ይህንን አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ ባለስልጣን መረጃዉን እንዳወጡት ነው በደፈናው መረጃዉን ግልጽ ባልሆነ መንገድ የጻፈው።
  • ዘገባው ግን ኢትዮጵያና ህወሓት በማለት ትግራይን እንደ አንድ የኢትዮጵያ አካል ያልሆነ ክልል አድርጎ ለመግለጽ የሞከረ ነው።
  • ድርድሩ በኬንያ እንደተጀመረና የህወሓት አመራርም የፌደራል መንግስትን አውቅና ለመቀበል በመስማማታቸው የተደረሰ ስምምነት እንደሆነም ገልጾ ድርድሩ አውን እንደሆነ አድርጎ ያቀረበ ዘገባ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ – https://theparadise.ng/breaking-ethiopia-tplf-reach-secret-deal-to-restore-electricity-banking-services-in-tigray-region/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *