Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ሕዳር 8፣ | 2015 ዓ.ም – Nov 17 | 2022

Africa news

 • በትግራይ ክልል ተጨማሪ ሰብአዊ እርዳታ  እየደረሰ ያለ መሆኑን የሚያሳይ የቪዲዩ የትንታኔ ዘገባ ነው 

የተነሱ ነጥቦች 

 • በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በትግራይ ክልል ሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግ የሚጠይቅ ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ ተጨማሪ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል  መድረሱን ።
 • ባለሥልጣናቱ እንዳሉት 14 የሰብአዊ ርዳታ መኪናዎች በትግራይ ክልል መድረሳቸውን ከእነዚህም መካከል በርካቶቹ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነዳጅ እና የምግብ ዕርዳታን ከዩኤን የዓለም የምግብ ድርጅት መሆናቸውን ።
 • የካቶሊክ ሚስዮናዊ አባት አልፍሬድ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ሆስፒታሎች በቂ የመድኃኒት አቅርቦት እያገኙ እንደሆነ መናገራቸውን ።
 • ትግራይ በከባድ ሰብአዊ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች ይህም ለሁለት ዓመታት በእርዳታ ላይ የተጣለው እገዳ ምክንያት እንደሆነ ።
 • እነዚህ ገደቦች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባለሙያዎች ቡድን የኢትዮጵያ መንግስት ምናልባት በአካባቢው ላይ ረሃብን እንደ ጦርነት ዘዴ ተጠቅሞበታል የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርስ መገፋፈቱን ።
 • በነበረው ጦርነት በትግራይ ብቻ 500,000 ሰዎች መፈናቀላቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል የድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ባወጣው ሰነድ  የሚያሳይ እንደሆነ ።
 • በትግራይ አካባቢውን በጎበኙ የዩኤን ቡድኖች የተፈናቀሉ ካምፖች ውስጥ ከረሃብ ጋር የተያያዘ ሞት ሪፖርት  መደረጉን ።
 • በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ክልሉ አሁንም የኢንተርኔት የስልክ እና የባንክ አገልግሎት ባይኖረውም አገልግሎቱን ወደ ትግራይ እንዲመለስ መጠየቁን ።

ሊንክ    https://www.africanews.com/2022/11/21/ethiopia-more-humanitarian-aid-arrives-in-tigray-region/

Today news Africa

 • ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ወደ 600,000 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆችን ለገደለው የኢትዮጵያ ጦርነት ህወሓትን  ተጠያቂ  ማድረጉን የሚተነትን ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • ወደ 600,000 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ለህልፈት ሞት የዳረገው ለሁለት አመት የቆየው ጦርነት መሆኑን ።
 • የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እንደተናገሩት ህዝቡን ለሞት እንዲደራግ ያደረገው ህወሓት መሆኑን እና ተጠያቂ  እንደሚሆን ።
 • ለሴማፎር ተብሎ በሚጠራው አዲስ የአሜሪካ ህትመት ላይ ባወጣው አስተያየት ኦባሳንጆ የሰላም ፈጣሪነት ሚናውን እና በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ያጋጠሙትን ችግሮች ።
 • በመንግስት እና በህወሓት መካከል በነበረው ጦርነት በአራት ክልሎች ማለትም በትግራይ በአማራ አፋር በኦሮሚያ ላይ እንደቀጠለ ። ።
 • ኦባሳንጆ አክለውም እንደ ኤርትራ እና ሱዳን ያሉ አንዳንድ የኢትዮጵያ ጎረቤቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጦርነቱ ውስጥ የበኩላቸውን ድርሻ ወስደዋል እና ሁሉም የቀንዱ ሀገራት በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውድቀቶች በተዘዋዋሪ  መጎዳታቸውን ።
 • ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት መልዕክተኛ እና የኢትዮጵያን የሰላም ድርድር በበላይነት  መቆጠቀጠራቸውን ።
 • ባለፉት አስራ አምስት ወራት ውስጥ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ሆኜ ሰላምን ደህንነትን እና መረጋጋትን ለማስፈን እየሰራሁ ነው ሲሉ መናገራቸውን ።
 • በተጨማሪም በስልታዊ አቋሟ እና በትግራይ ክልል የተነሳው ግጭት ትኩረቱ እና ፍፃሜው ኢትዮጵያ እንደሆነች ።

ሊንክ    https://todaynewsafrica.com/olusegun-obasanjo-blames-tplf-for-ethiopias-war-that-killed-nearly-600000-tigrayans-says-peace-accord-must-be-implemented-and-reconstruction-will-c

  Sudan tribune

 • የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣን በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መወያየታቸውን የሚዘግብ ጽሁፍ ነው

የተነሱ ነጥቦች

 • የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢጋድ ሀገራትን እየጎበኙ ከሚገኙት የሱዳን ወታደራዊ መሪ የሽግግር ምክር ቤት አባል ኢብራሂም ጋቢር ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ  መወያየታቸውን ።
 • የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና በጄኔራል ጋቢር የተመራ የሱዳን ልዑካን ቡድን በሁለትዮሽና በሁለቱ ሀገራት ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ።
 • ስብሰባው የሱዳን እና የኢትዮጵያ የስለላ ኤጀንሲዎች በሁለቱ ሀገራት መካከል በፀረ ሽብር እና ወንጀል ላይ የመረጃ ልውውጥን ለማሳደግ ስምምነት መፈራረማቸውን ።
 • የኢትዮጵያ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ድንቁ በካርቱም ያደረጉትን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ማጠናቀቃቸውን
 •  የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከሱዳኑ አቻቸው አህመድ ኢብራሂም ሙፋዳል የኢንተለጀንስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጋር መወያየታቸውን  ።
 • የሱዳን ምክትል ወታደራዊ መሪ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ከኢትዮጵያ ባለስልጣን ጋር  መገናኘታቸውን ።
 •  የኢትዮጵያ መረጃ ዳይሬክተር ለጄኔራል ዳግሎ በፌዴራል መንግስት እና ህወሀት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ስለ ሀገራቸው ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ  ማድረጋቸውን ።
 • በሱዳን የኢጋድ ሊቀመንበር የምስራቅ አፍሪካ ህብረት በፀጥታ፣ በኢኮኖሚ ውህደት እና ከባህላዊ ካልሆኑ አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር ለማስፋት በሱዳን የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ አስመልክቶ አቶ ጋቢር ለአህመድ ማብራሪያ  መስጠታቸውን ።

ሊንክ   https://sudantribune.com/article267099/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *