የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም 18፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 28 | 2022
Africa times
- አሜሪካ የፌደራል መንግስትን እና ህወሓት በአፍሪካ ህብረት የሚመራ ድርድር ላይ እንዲሳተፉ ማሳሰቧን የሚተነትን ነው ።
የተነሱነጥቦች
- የአሜሪካ መንግስት የፌደራል መንግስትን እና የህወሓትን ሀይል መካካል ያለውን ጦርነቱን ኤርትር መውጣት እንዳለባት ።
- የአሜሪካ መንግስት እንዳሳሰበው መንግስት እና የህወሓት ሀይል የሰላም ድርድር እንዲያደርጉ በድጋሜ መናገሯን ።
- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንደተናገሩት ለሁለቱም ወገን አለመደገፉን ።
- ነገር ግን የፌደራል መንግስት የሚያስበው አሜሪካ ህወሓትን እንደምትደግፍ አድርጎ ነው የሚያስብው የሚለውን ማስተባበሉን ።
- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንደሚሉት ከሆነ የአፍሪካ ኅብረት በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶቹ የተቃጣውን ሁከትና ብጥብጥ ለማስቆም እኛ የተቻለንን እያደረግን ነው ማለታቸውን ።
ሊንክ https://africatimes.com/2022/09/27/u-s-urges-ethiopia-tplf-to-engage-in-au-l
Reuters
- በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል አከባበር ላይ የጦርነት ጥላ ታይቶል መባሉን የሚያብራራ የቪዲዮ ዘገባ ነው ።
የተነሱነጥቦች
- በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል ላይ የጦርነት ጥላ እንደነበረ የሚገልፅ ዘገባ እንደሆነ
- የዘንድሮ የመስቀል በዓል ከፍተኛ ጥበቃ ብዙ ሕዝብ የተገኘበት እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ካህናት በስብከታቸው ሰላምና ይቅርታ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ።
- የመስቀል በዓል 4ኛው ክፍለ ዘመን የሮማውያን ንግሥት ቅድስት ሄለና የክርስቶስን መስቀል በኢየሩሳሌም ያገኘችበትን ጊዜ እንደሚያመለክት ።
- ከዓመት ዓመት እንደሚያደርጉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ካህናት፣ ሙዚቀኞችና ዘማሪዎች ነጭ ካባ ለብሰው በመዲናዋ መስቀል አደባባይ ሰፊ ቦታ ላይ መሰብሰባቸውን ።
- በእውነት ዘንድሮ እኛ ኢትዮጵያውያን በዓሉን በደስታ እያከበርን እንዳልሆነ እና ስሜቱ ጨልሞ ስለነበር የሃይማኖት አባቶች በትግራይ ክልል ያለውን የግጭት ሁኔታ በማስታወስ ሰላም እንዲኖር መጠየቃቸውን ።
ሊንክ https://www.reuters.com/world/africa/shadow-war-hangs-over-ethiopias-meskel-fest
- በተጨማሪ የሳተላይት ምስሎች በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ማክስር ወታደራዊ መገንባታቸውን እንደሚያሳዩ የሚዘግብ ዘገባ ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የሳተላይት ምስሎች በዚህ ወር እንሚያሳየው በትግራይ ድንበር እና በኤርትራ መካካል በሚገኙ ከተሞች የሚካሄደውን ወታደራዊ ሀይል ቅስቀሳ እንደሚያሳዩ የአሜሪካ የግል ኩባንያ ማሳወቁን ።
- በትግራይ ክልል ለአምስት ወራት የተኩስ አቁም ስምምነት መፈራረሱን ተከትሎ የተዘገበው ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ምስሎችን ይዘት ሮይተርስ በገለልተኝነት ማረጋገጥ አለመቻሉን ።
- መንግስት እና አጋሮቹ የኤርትራን ወታደሮች የህወሓትን ሀይል ለሁለት አመት ሲዋጉ መቆየታቸውን ።
- በትግራይ እና የኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ሽራሮ ከተማ ወታደራዊ ሃይሎችን ተሸከርካሪዎችን እና የመድፍ ቦታዎችን ማሳየቱን ማክስር ቴክኖሎጂስ ኢንክ ስለ ክልሉ የሳተላይት ምስሎችን ሰብስቦ መናገሩን ነው ።
- ከኤርትራ የተነሱት ምስሎች እንደሚያሳዩት በትግራይ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ሰርሃ ከተማ ከባድ መሳሪያ መሰማራቱን ያሳያል ሲል ማክስር መናገሩን ።
- የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለስልጣናት በሰሞኑ ጦርነት ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸስውን ።
ሊንክ https://www.reuters.com/world/africa/satellite-images-show-military-build-ups-ethiopia-erit