የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
መስከረም 13፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 23 | 2022
Voa
- በኢትዮጵያ ኦሮምያ ክልል እየተከሰተ ያለው ብጥብጥ በሺዎች የሚቆጠሩ መፈናቀል እንዳለ ቪዲዩ የሚተነትን ነው
የተነሱ ነጥቦች
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን መግለፁን ።
- አማፂው የሸኔ ሀይል ከሰኔ ወር ጀምሮ ጥቃት እየፈፀመ ሲሆን የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ደግሞ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በደል ሲፈጽሙ መቆየታቸውን ።
- በዘገባው እንዳየነው ሄንሪ ዊልኪንስ በደብረ ብርሃን የሚገኘውን የተፈናቃይ ካምፕ መጎብኝታቸውን ።
- ከተፈናቀሉት ውስጥ አንዳንዶቹ እንዳሉት ግጭቱን ሸሽተው የተመለሱትን ሲናገሩ በየቀኑ አዲስ መጤዎች እየመጡ እንደአሉ ነው።
ሊንክ https://www.voanews.com/a/spiraling-violence-in-ethiopia-oromia-region-sees-thousands-
European times
- የአማራ ቤሔር ላይ እይተፈፀመ ያለው የተደበቀ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚል ትንተናነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት ሀይሎች መካከል የሰላም ድርድር እየተካሄደ ባለበት በዚህ ወቅት የአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለ ግድያ ።
- የኢትዮጵያ አንጋፋ በሆኑት የአማራ ተወላጆች ላይ ስልታዊ እና ሆን ተብሎ የተደረገው ግድያ አሁንም በቸልተኝነት እየተፈፀመ እንደሆነ ።
- በዚህ ግጭት ወቅት ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የሲቪል ማህበረሰብ ከፍተኛ ስም ያላቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እዚህ ውግዘት ላይ መሳተፋቸውን ቁርጠኛ መሆናቸውን ።
- በስዊዘርላንድ የአማራ ዘር ማጥፋት ይቁም በሚል እና ማንኛውንም አይነት መድሎ ለመታገል ቁርጠኛ መሆናቸውን ።
- የአማራ የዘር ማጥፋት ይቁም ከሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በመሆን በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ውስጥ እየደረሰ ስላለው የአማራ የዘር ማጥፋት ግንዛቤ ለመፍጠር እና እነዚህን እኩይ ተግባራት ለማስቆም እንደሚሰራ ።
- አለማው የአማራን ዘር ላማጥቃት በሁሉም ክልል ላይ ለተነሳው የአማራን የዘር ማጥፋት ስራ የሰባዊ መብት ተሞጋች ጨምሮ እየሰራ እንዳልሆነ
- ነገር ግን የአለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ሚዲያዎች ይህንን የዘር ማጥፋት ዘገባ ላለመዘገብ የመረጡት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሀይላቸውን በመቀላቀል የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቁም የሚል ማህበር እንዲፈጠር ምክንያት እንደሆነ ነው ።
- የማህበሩ ዳይሬክተር እና መስራች አባል ወይዘሮ ዮዲት ጌዲዮን ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በማህበሩ አመራር ላይ ሲሆኑ ማህበሩ ከሩዋንዳ እና ፈረንሳይን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የቦርድ አባላት እንዳሉት ።
ሊንክ https://www.europeantimes.news/2022/09/amharas-the-occulted-ongoing-genocide-in-ethiopia/
UN News
- በትግራይ ሰላማዊ ዜጎች እንደገና ወደ ማይፈታ እና ገዳይ ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ መስማቱን ።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ህዝብ በመንግስት ወታደሮች እና በህወሓት ሀይል መካከል በተፈጠረው ግጭት እንደገና በማይታለፍ እና ገዳይ መዘዞች ውስጥ እንደወደቀ የመብት ተመራማሪዎች ማሳወቃቸውን ።
- የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ ላይ በሰሜናዊ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነትም በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ብለው እንደሚያምኑ መናገራቸውን ።
- በትግራይ ከባድ የመብት ጥሰቶች በመቀጠል ላይ ናቸው ሲል ዘገባው አክሎ መግለፁን
- የአምስት ወራት የተኩስ አቁም ስምምነትን በኋላ ውጊያው ባለፈው ወር እንደገና መቀስቀሱንና ማስታወቃቸውን ።
- የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት እንዳስታወቀው በጦርነቱ ምክንያት ከህግ-ወጥ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ጾታዊ ጥቃት እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ረሃብ እና ጦርነት በኢትዮጵያ ግጭቱ ከጀመረበት ጀምሮ መከሰቱን ለምክር ቤቱ ማሰማቱን ።
ሊንክ https://news.un.org/en/story/2022/09/1127481
Africa news
- በትግራይ ዋና ከተማ የአየር ጥቃት አንድ ሰው መግደሉን የያዘ ዘገባ በቪዲዩ መልክ መቅረቡን
የተነሱ ነጥቦች
- በመቀሌ ከተማ በደረሰ የአየር ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ማስታወቁን ።
- ዛሬ ጠዋት እረፋድ ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ማድረሱን ።
- በመቀሌ በነበረው ግጭት የ60 አመት አዛውንት መገደላቸውን በመቀሌ የአይደር ሆስፒታል ሀላፊ የሆኑት ክብሮም ገብረስላሴ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ መናገራቸውን ።
- ይህ ጥቃት የደረሰው በመቀሌ ከተማ ደስታ ሆቴል አካባቢ በሰው አልባ አውሮፕላን በደረሰ ጥቃት የሞተ አስከሬን አይደር ሆስፒታል መድረሱን ሆስፒታሉ በትዊተር ገፁ ላይ ማስታወቁን ።
- የኢትዮጵያ መንግስት ወታደራዊ ኢላማዎችን ብቻ እንደሚያጠቃ እና የህወሓት ሀይሎች የዜጎችን ህይወት እንዲቀጥፉ በማድረግ ላይ መሆኑን በየጊዜው የሚታይ መሆኑን ።
- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጦር ሰራዊቱን ልከው በህወሀት ሀይሎች ካምፖች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል በሚል መከሰሳቸውን ።
- አሁን ላይ ያለው ጦርነት የሰላም ድርድርን ጠባብ ተስፋ ማጨለሙን ።
ሊንክhttps://www.africanews.com/2022/09/23/ethiopia-one-killed-in-air-strike-on-tigray-capital/