የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም 8፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 18 | 2022
Reuters
- በኢትዮጵያ ጦርነት ለመሳተፍ ኤርትራ ለሰራዊቷ ጥሪ እንዳቀረበች የካናዳ መንግስት መግለፁን የሚመለከት ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- በመንግስት እና በህወሓት መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ኤርትራ የታጣቂ ሃይሎችን በማሰባሰብ ላይ እንደምትገኝ የካናዳ መንግስት መግለፁን ።
- በህወሓት ሀይሎች የተነሳው ጦርነቱ ሊባባስ ይችላል በሚል ስጋት በሰሜን ክልል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለ እና ሰብአዊ አደጋን ማስከተሉን ።
- የህወሓት ሀይሎች ኢትዮጵያ ለተፈጠረው ግጭት ምላሽ የታጠቁ ሃይሎችን ለማሰባሰብ አጠቃላይ ጥሪ ማቅረባቸውን መናገራቸውን የካናዳ የጉዞ ምክር በትዊተር ገጹ መዘገቡን ።
- የካናዳ መንግስት በኤርትራ የሚገኙ ዜጎቹ እንቅስቃሴያቸውን እንዲገድቡ እና የሀገር ውስጥ ሚዲያዎችን እንዲከታተሉ ማሳሰቡን ።
- የአፍሪካ ቀንድ ዲፕሎማት ለሮይተርስ እንደተናገሩት “በኤምባሲዎች፣ በዩኤን ግቢዎች እና መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ያሉ ጠባቂዎች ሰፊ በሆነው የውትድርና ግዳጅ ከሃላፊነታቸው ይወሰዳሉ የሚል ስጋት እንደነበራቸው ።
ሊንክ https://www.reuters.com/world/eritrea-issues-army-mobilisation-call-ethiopia-fighting-resumes-
Egypt independent
- የህወሓት ሃይሎች አፋጣኝ የተኩስ አቁም እና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መቀበላቸውን የሚተነትን ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የህወሓት ሀይሎች ጦርነቱን ለማቆምና እና የሰላም ድርድር ለማድረግ በአፍሪካ ህብረት የሚደርገውን የሰላም ጥሪ ለመቀበል ዝግጁ እንደሆኑ ማስታወቃቸውን ።
- ህወሓት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በአፋጣኝ እና በጋራ ስምምነት ላይ የሚደርሰውን ጦርነት ለማቆም ዝግጁ ነን ሲል በመግለጫው መግለፃቸውን ።
- የህወሓት ተደራዳሪ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ሳይዘገዩ ለመሰማራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግሯል ።
- የፊደራል መንግስት በሰኔ ወር ከህወሓት ሀይሎች ጋር ለመደራደር ኮሚቴ ማወቀራቸውን ።
- የአፍሪካ ኅብረት የሕወሃትን መግለጫ በደስታ መቀበሉን ።
- የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ሰላም ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለስ የሚያስችል ልዩ አጋጣሚ ነው ሲሉ መናገራቸውን ።
- ህወሀት ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ህብረት ሽምግልና ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደነበረው መግለፁን ።
- የህወሓት ሀይል ከመንግስትን ጋር ድርድር የሚያደርግው እንደ ባንክ እና ግንኙነት ያሉ ዋና ዋና አገልግሎቶችን ወደ ትግራይ እንዲመልስ መጠየቁን ።
- የፌደራል መንግስት ግን የአፍሪካ ህብረት ጣልቃ ከመግባቱ በፊት ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ መኖር እንደሌለበት ማሳሰቡን ነው ።
ሊንክ https://www.egyptindependent.com/tigrayan-forces-accept-immediate-ceasefire-and-au-
VOA
- የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ሰራዊት መጥራቱን የሚተነትን ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኤርትራ ባለስልጣናት በሰሜናዊ ክልል ዳግም ለተቀሰቀሰው ጦርነት ምላሽ ለመስጠት የታጠቁ ሀይሎቻቸው እንዲንቀሳቀሱ መጠየቃቸውን የእንግሊዝ እና የካናዳ መንግስታት ማሳወቃቸውን ።
- በመንግስት እና በህወሀት መካከል ለሁለት አመታት የዘለቀው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የነበረውን ተስፋ መጨለሙን ።
- የህወሓት ቡድን የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ጦርነቱ እንደገና መነሳቱን እና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ ውይይት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ።
- የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ቁርጠኛ ነኝ ከማለት ውጪ ለደረሰው ተቃውሞ በይፋ ምላሽ አለመስጠቱን ።
- ይህን ጦርነቱ ማን እንደ ጀመረው ሁለቱም ወገኖች አለመናገራቸውን እና ጦርነቱ ከደቡብ ትግራይ አከባቢ ወደ ሰሜን እና ምዕራብ ራቅ ካሉ ግንባሮች አሁን ላይ መዛመቱን
- በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያን ጦር ይደግፉ የነበሩ የኤርትራ ወታደሮችን ወደ ውስጥ መግባቱ እንደሚታወስ ።
ሊንክ https://www.voanews.com/a/eritrea-calls-up-armed-forces-after-ethiopia-clashes-