የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
መስከረም 7፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 17 | 2022
BBC
- በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ኤርትራ ከፍተኛ የተሳትፎ እንቅስቃሴ አለ የሚል ጽሁፍ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- ኤርትራ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባለው ጦርነት የፌድራል መንግስትን ጦር በውግያ ለማገዝ ከፍተኛ ጦር ማንቀሳቀስ እንደጀመረች።
- በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና ህወሓት ጦርነት ለመሳተፍ ኤርትራ ከፈተኛ ጦር በማንቀሳቀስ እንዲሁም ዜጎችን በግዴታ ወደ ጦርነት እያስገባች እንደሆነ
- እስካሁን በኢትዮጵያ በነበረው ጦርነትም የኤርትራ ጦር ተሳታፊ እንንደነበር የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ https://www.bbc.com/news/world-africa-62927781
VOA NEWS
- የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢትዮጵያ የሰላም ሂደትን ሊመሩ እንደሆነ የሚተነትን ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የኢትዮጵያ የሰላም መልዕክተኛ አድርገው እንደሾሟቸው።
- ይህ የኬኒያ የቀድሞ መሪ ከዚህ በፊትም የሠላም ጥረቶች ላይ ተሳትፎ እድርገው እንደነበር
- አሁንም የማደራደር ሚናቸውን ለመወጣት የሚሠሩት በኬኛ በኩል እንደሆነ የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ https://www.voanews.com/a/former-kenyan-president-to-lead-peace-process-in-drc-ethiopi
All Africa
- የኢትዮጵያ ሃይሎች በትግራይ ላይ የድሮን ድብደባ በማድረግ እሸብረዋቸዋል የሚል ጽሁፍ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ አየር ሀይል በህወሓት ጦር ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን
- በሁለት የድሮን ድብደባ እርምጃ 10 የሚሆኑ ሠዎች መሞታቸውን
- መረጃዉን ለሚዲያ የሠጠውም በመቀሌ አይደር ሆስፒታል የሚሠራ የህወሓት አባል እንደሆነ
- የኤርትራ ጦር በዚህ ጦርነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እየሠራ እንደሆነ
- ትክክለኛ እውነታን የሚያመላክቱ መረጃዎችን የማሠራጨት ሥራን መሥራት አለበት።
ሊንክ https://allafrica.com/stories/202209170007.html