የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ጳጉሜ 2፣ | 2014 ዓ.ም – SEP 7 | 2022
Africa news
- የአሜሪካ ልዑክ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግጭት ለማስቆም እየሞከሩ እንዳሉ ነው የጻፍው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም እና የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመጥራት በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚመጡ ማስታወቃቸው
- ለወራት የዘለቀውን የተኩስ አቁም በማፍረስ ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን መጀመራቸው
- ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት ለሰላም ድርድር ያለውን ተስፋ ቆርጦ ግጭቱ እንዳይስፋፋ ስጋት መፍጠሩ
- የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሚስተር ሀመር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የሚገልጹ ዋና ዋና ነጥቦች አሉት
ሊንክ https://www.africanews.com/2022/09/06/us-envoy-in-ethiopia-to-halt-ongoing-conflicts/
Alarabiya news
- በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በዘር ላይ በተመሰረተ በደርሠው ጥቃት 60 ሰዎች መሞታቸውን በግለጹን የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በዘለቀው የብሔር ተኮር ጥቃት ታጣቂዎች ከ60 በላይ ሰዎችን መግደላቸው
- በተጨማሪም ከ20,000 በላይ መፈናቀላቸውን የሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መናገሩ
- በኢትዮጵያ ትልቁ ብሄር የያዙት ኦሮሞ እና አማራ መሆናቸውን የታወቀ ቢሆንም እነዚህ ብሄርሰቦች ከቅርብ ጌዜ ወዲ እርስ በእርስ በፖለቲካዊ ውዝግቦች እየተባባሰ የሚሄድ ብጥብጥ መታየቱ
- የሸኔ ተዋጊዎች የኦቦራ ከተማን ለመያዝ አድርገዋል በማለት ለዚያም ሙከራ ባደረጉበት ወቅት በሂደቱ ሶስት የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን ማስታወቁ
- በሁለት ቀናት በዘለቀው ጥቃት ከ60 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ70 በላይ መቁሰላቸው
- በተነሳው ግጭት ንብረትና ከብቶች ተዘርፈዋል ሲል የኢሰመጉ የአካባቢውን ሰዎችና ባለሥልጣናትን ጨምሮ መግለፁን ነው ።
- በዚህ ግጭት ምክንያት ከ20,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለው በኦቦራ ከተማ እንደገኙ መናገራቸው የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ https://english.alarabiya.net/News/world/2022/09/06/Ethnic-attacks-kill-60-in-Ethiopia-s
Sudan tribune
- ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም የምታደርገው ቀጣናዊ ጥረት እንደቀጠሉበት ነው ትንተና ያቀረበው።
የተነሱ ነጥቦች
- ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም ቀጠናዊ ጥረቶችን አጠናክረው በመቀጠል ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላቸውን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ መገለጹ
- የደቡብ ሱዳን የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪ ቱት ጋትሉክ ማኒሜ ለሱዳን ትሪቡን በሰጡት መግለጫ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር እና የሱዳኑ አቻቸው ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ግጭቱን ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት ሁሉ እንደሚደግፉ መናገራቸው
- ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያ በፀረ-ሽብርተኝነት ትግል ውስጥ ያላትን ሚና ማመናቸው
- ሁለቱ መሪዎች እንደተናገሩት መንግስት እና ህወሓት ወደ ነበሩበት ለመመለስ እና እንዲሁም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቀዳሚዎቹ መሆናቸውን መግለጻቸውን የሚገልጹ ዋና ዋና ነጥቦች አሉት
ሊንክ https://sudantribune.com/article263733/