የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 27 ፣ | 2014 ዓ.ም – SEP 2 | 2022
VOA
- ህወሓት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኤርትራ ሃይሎች ከፍተኛ ጥቃት ተፈጽሞብኛል ማለቱን የሚተነትን ።
የተነሱ ነጥቦች
- የህወሓት ሀይሎች እና የኤርትራ ወታደሮች መካከል ግጭት መጀመሩን ህወሓት መግለጹ
- የህወሓት ቃል አቀባይ በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የኤርትራ ሃይሎች ከህወሓት ጋር በመዋጋት የኢትዮጵያ ፌደራል ሃይሎችን መቀላቀላቸው
- በምእራብ በኩል አዲያቦ አካባቢ ከፍተኛ ጦርነት መነሳቱን እና የኤርትራ ወታደሮችም እንዳሉበት በመጥቀስ መናገራቸውን ።
- በተጨማሪም የህወሓት ሃይሎችም በመከላከል ላይ መሆናቸውን መግለፃቸው
- የህወሓት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆኑ አውሮፕላኖች ወታደራዊ ሰዎችን ለማጓጓዝ እና የጦር መሳሪያ ለማቅረብ በሰሜን ለሚገኙ ወታደሮች እየዋሉ ነው ማለታቸው
ሊንክ- https://www.voanews.com/a/tplf-reports-massive-offensive-by-ethiopian-government-eritrean-tml
Bloomberg
- የኤርትራና ኢትዮጵያ ሰራዊት ጥምር ጥቃት እንደፈፀሙበት የህወሓት ሀይል መክሰሱን የሚተነትን ነው
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሰራዊት በሰሜናዊ ትግራይ ክልል በአራት አካባቢዎች ማጥቃት መጀመራቸውን የህወሓት ከፍተኛ አመራር መግለፃቸው
- ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተባብረው ጦርነቱን ወደ ክልላዊ ግጭት ለመቀየር ጥረታቸውን እያስተባበሩ እንደሚገኙም ህወሓት መግለጹ
- የህወሓት ሀይሎች ጦርነቱን ቢቀጥልም እኛም እራሳችንን ለመከላከል ዝግጁ ነን ማለታቸው
- ኤርትራ ግጭቱን መቀላቀሏ ግጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ መባባሱን የሚያመለክት እንደሆነ ።
- ባለፈው ከሱዳን ድንበር አቋርጦ የመጣውን የጦር መሳሪያ አውሮፕላን በመንግስት ወታደሮች መመታቷን የህወሓት አመራሮች ማንሳታቸው
ሊንክ https://www.bloomberg.com/news/articles/2022-09-01/eritrea-joins-offensive-in-ethiopia-s-tigray–
Reuters
- በመንግስት እና በህወሓት መካከል ለምን ጦርነት እንደገና እንደተጀመረ ነው የጻፈው
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስት ወታደሮች በህወሓት ሀይሎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸው
- ህወሓት ግጭቱ የተነሳው ለስምምነት ከተዘጋጁ በኋላ ጦርነቱን መጀመራቸውን እና አሁን ላይ ጦርነቱ ሁለተኛ ሳምንቱን መያዙ
- የኢትዮጵያ መንግስት በተፈጠረው ጦርነት በህወሓት አማፂ ሃይሎች ለጥቃት ተጠያቂ መሆኑን በመግለጽ የማጥቃት እርምጃቸውን መቀጠላቸው
- አህን ጦርንቱ እንደ አዲስ የተቀሰቀሠው ኤርትራ ሁለቱን ወገኖች ማለትም የፌደራል መንግስትንና የህወሓትን ሀይል ወደ ግጭት እንዲገቡ በመገፋፋት የተነሣ እንደሆነ
ሊንክ https://www.reuters.com/world/africa/tplf-says-ethiopian-eritrean-forces-attack-northwest-tigray-