የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 24 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 30 |2022
VOA
- የህወሓት ሃይሎች በአማራ ክልል ወልዳያን እንዳልያዙ ነው የጻፈው
የተነሱ ነጥቦች
- ከአምስት ወራት ቆይታ በኋላ በህወሓት እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱ
- አንዳንድ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ወያኔ በአማራ ክልል ወልድያ ከተማ መግባቱን እየዘገቡ መሆናቸው
- የህወሓት ተወካይ ለቪኦኤ እንደተናገሩት የህወሓት ሀይሎች እስካሁን ወደ ከተማዋ አለመግባታቸውን ይህ አባባል ውሸት እንደሆነም መናገራቸው
- አሁን ላይ ያለው ዋና ግጭት ከሰሜን ራቅ ባለ የቆቦ ከተማ ዙሪያ እንደሆነ የሚሉት አንኳር ነጥቦች ናቸው
ሊንክ https://www.voanews.com/a/tigrayan-forces-deny-taking-town-in-amhara-region-
Tele SUR English
- የመብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም መጠየቃቸው ላይ የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ግጭቱን በአስቸኳይ አቁመው ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረባቸው
- ፓርቲዎች ትግላቸውን ባስቸኳይ አቁመው እያንዳንዳቸው ወደተቀበሉት የውይይት ሂደት እንዲመለሱ መጠየቃቸውን ።
- ይህ ግጭት በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር እንደሚያባብስ እና የከፋ አደጋም እንደሚያስከትል ማሳሰባቸው የሚሉት አንኳር ነጥቦች ናቸው
ሊንክ https://www.telesurenglish.net/news/Rights-Defenders-Call-for-Cessation-of-Hostilities-in-
Sudan Tribune
- የሕወሃት ሃይሎች ከተሞችን በውግያ መያዛቸውን ምንጮች የተገለጸ መሆኑን ነው የተጻፈው
የተነሱነጥቦች
- አሸባሪው ህወሓት መጠነ ሰፊ ጥቃትን ከፍቶ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ በርካታ ከተሞችን እንደወሰደ እንዳለ እና ግጭቱ ወደ ሌሎች ከተማ ሊያመራ የሚችል እንደሆነ
- ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዓለም አቀፍ ጫናዎች በፈጠሩበት ወቅት የተደረሰውን የሰብአዊ እርቅ ስምምነት መጣሳቸውን እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ መሆናቸውን
- የህወሓትን ሃይሎች ወደ አጎራባች የአማራ ክልል ግዛቶች በመግባት የቆቦ እና የሮቢት ከተሞችን ጨምሮ ስምንት ከተሞችን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ መናገራቸው
- የመንግስት ሀይሎችም ውግያ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀጣጠሉ ከያዙበት ቦታዎች እያፈገፈጉ እንደሆነ የሚሉት አንኳር ነጥቦች ናቸው
ሊንክ – https://sudantribune.com/article263419/
Egypt independent
- ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ላይ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን እንደሳወቀች የተጻፈ ነው።
የተነሱነጥቦች
- ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንዳላት መግለትጿ
- በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል ኤመሮ በግድቡ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በወንድማማችነት መፍታት እንደሚቻል መናገራቸው
- የግድቡ የውሃ ማጠራቀሚያ ሶስተኛውን ሙሌት በተመለከተ የኢትዮጵያ አምባሳደር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ማረጋገጣቸው
- በዚህ ሙሌት ላይ ሱዳንም እንደማትጎዳ እና በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ሱዳን እና ግብፅ ላይ ምንም አሉታዊ ተጽእኖዎች አለመኖራቸው
- ከቀናት በፊት ካርቱም በአባይ ግድብ 20 ሚሊዮን ሱዳናውያንን አሉታዊ በሆነ መልኩ ይጎዳል በማለት ብትናገርም ይህ የሦስተኛው ሙሌት ሙሌት በሱዳን የጎርፍ አደጋን እንደቀነሰ የሚሉት አንኳር ነጥቦች ናቸው
ሊንክ https://egyptindependent.com/ethiopia-says-ready-to-negotiate-with-egypt-sudan-over-gerd/