የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ነሐሴ 14 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 20 |2022
Bloomberg
የህወሓት ቡድን የፌደራል መንግስት ጦርነት ከፍቶብኛል ሲል መክሰሱን ነው ያስተጋባው።
የተነሱ ነጥቦች
- እየተፈጠረ ያለው የሁሉቱም ወገን የእርስ በእርስ መወነጃጀል እስካሁን የሠላም ስምምነት ላይ እንዳይደረስ ማድረጉ
- በቅርድቡ የመንግስት መከላከያ ሠራዊት በቦምብ ጥቃት አድርሶብኛል ሲል መክሰሱ
- ኢትዮጵያን ከሱዳን ጋር የሚያዋስነው ሰፊ ለም የእርሻ መሬት ምዕራብ ትግራይ ከጎረቤት የአማራ ክልል በመጡ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
ሊንክ – https://www.bloomberg.com/news/articles/2022-08-19/flare-up-in-ethiopia-tensions-dulls-
Reuters
በትግራይ ውስጥ የክልሉን ህዝብ ግማሽ የሚሆኑ ዜጎች የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዳሳወቀ የሚዘግብ ነው።
የተነሱነጥቦች
- በትግራይ ክልል የእርዳታ መጠን ከህዝቡ ቁጥር ጋር የማይመጣጠን እንደሆነ
- የመሠረታዊ አገልግሎቶች መቋረጥ የህዝቡን ችግር እንዳባባሰ
- በክልሉ የህክምና እጥረትም በከፈተኛ ሁኔታ እየተስተዋለ እንደሆነ
- ሥላምን ለማስፈን ሁለቱ አካላት እንዲደራደሩ ለማድረግ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ቢኖሩም ያለው ሁኔታ የድርድሩን ስኬት ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት እየሆነ እንዳለ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
ሊንክ – https://www.reuters.com/world/africa/nearly-half-people-ethiopias-tigray-need-food-aid-