የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 13፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 19 |2022
VOA
- ህወሓት “ መንግስት ጥቃት ከፍቶብኛል በማለት ከሷል “ በማለት ሀሳቡን ያስተግባ ጽሁፍ ነው።
የተነሱነጥቦች
- የህወሓት ሀይል ለወራት የቆየው የተናጠል የተኩስ አቁሙ እንደፈረሠና ያም በመንግስት በመሆኑ አዲስ ጦርነት እክፍታለሁ ማለቱ
- አንድ ፍሰሐ አስግዶም የተባለች የህወሓት ቃአቀባይ ነኝ ያለች ሴት ለሚዲያ መንግስት በተለያዩ ቦታዎች በቦምብና በሌሎች ከባድ መሥርያዎች ውግያን በህወሓት ላይ እንደከፈተ መናገሯ
- መንግስት ድርድር አደርጋለሁ እያለ ቢሆንም በመዘግየቱና እውነት ከሆነ በተባሉ የጦርነት ትንኮሳዎች የሠላም በር ላይከፈት እንደሚችል መገለጹ የሚሉት ዋና ዋና የጽሁፉ ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.voanews.com/a/tplf-alleges-government-attacks-in-ethiopia-s-tigray-region-l
Sudan Tribune
- የኢትዮጵያ መንግስት ህወሓት መንግስት “የተኩስ አቁሙ አፈረሰው “ የሚለውን በማስተባበል ለህጋዊ የጋራ የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሪ አቅርቧል ይላል።
የተነሱነጥቦች
- ህወሓት መንግስት ተኩሶብኛል ለሚለውን ክሥ መልስ በመስጠት ህወሓት የሠላም ድርድሩ በምደናቀፍ ለጦርነት ባለው ፍላጎት የተነሳ ይህን ፕሮፓጋንዳ መጀመሩን መግለጹ
- ሀሓትም መንግስት ሠላም እንዲሰፍን አይፈልግና በትግራይ እመልሳለሁ በማለት የገባውን ቃል ተላልፏል በማለት ክሥ ማቅረቡ
- መንግስት የህወሓትን ውንጀላ እንደማይቀበልና ለሠላም ድርድሩ አሁንም ዝግጁ መሆኑን መግለጹ
- ድርድሩ እስካሁን ሊዝገይ የይ የቻለውም በሁለቱም በኩል ያሉት ያለመተማመን ሁኔታዎች የተነሳ እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
ሊንክ – https://sudantribune.com/article262960/
Reuters
- የትግራይ ሀዝብ አጋማሽ የሚሆን ቁጥር ያለው ህዝብ ባሁኑ ሰዓት የምግብና የጤና አገልግሎቶች እርዳታ እንደሚያስፈልገው ነው የጻፈው።
የተነሱነጥቦች
- በክልሉ የነዳጅ እጥረት የተነሳ ለክልሉ ህዝብ እርዳታን የማክፋፈል ሥራን ለመሥራት የእርዳታ ሠራተኞች እንደተቸገሩ
- እስካሁን የገባው እርዳታ መንግስት በራሱ በኩል ተኩስ ካቆመ በኋላ መሆኑ
- አሁንም በክልሉ ከፍተኛ የረሀብ አደጋ መኖሩን
- ድርድሩም እስካሁን በሁለቱም ወገኖች ለድርድር ፍላጎት እንደሌለ በመግለጽ የማከሰሥ ሁኔታዎች የተነሳ መዘግየቱና አሁን ለመሳካቱ አጠራጣሩ ደረጃ ላይ መድረሱ
ሊንክ- https://www.reuters.com/world/africa/nearly-half-people-ethiopias-tigray-need-food-aid-19/