የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
![](https://ethiopiantruth.com/wp-content/uploads/2022/08/12h.png)
ነሐሴ 12፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 18 |2022
Aljazeera
- መንግስት በትግራይ ሠላም እንዲሰፍን እንደሚፈልግ የሠላም ማውረድ ሀሳብ እንዳቀረበ ነው የጻፈው።
የተነሱነጥቦች
- መንግስት ከህወሓት ጋር በስምምነት የተደገፈና ሁለቱንምም ወገን ያካተተ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረሰ እንደሚፈልግ መግለጹ
- የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ምንም አይነት የውይይት ፍላጎት አላሳየም በሚል ህወሓት የኮሚቴውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብ አለመቀበሉን መግለጹ
- የመንግስት ወታደሮች / መከላከያ የጦርነት ፍላጎት እንዳለውና ትንኮሳ እያደረገብን ነው ሲል የህወሓት ቃላቀባይ ጌታቸው ረዳ ትዊተር ላይ መጻፉ
- የዓለም ጤና ድርጅር ውና ዳይሬክትሩ ዶክተር ቴድሮስ አድኀኖም የትግራይ ችግር ሆን ተብሎ የተደረገና የመንግስት የጭካኔ ድርጊት እንደሆነ አድርጎ መግለጹ
ሊንክ – https://www.aljazeera.com/news/2022/8/17/ethiopia-government-proposes-plan-for-peace-
AP News
- ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ በትግራይ ላይ የሰጡት አስተያየት “ሥነ ምግባር የጎደለው ነው” በሚል እንዳጣጣለችው ነው የሚተርከው።
የተነሱነጥቦች
- ዶክተር ቴድሮስ ጉዳዩ የዓለምን ትኩረት ያጣና ሆን ተብሎ መፈጸሙን የሚያሳይ ነው ማለቱ
- መንግስት ግለሠቡ ራሱ የትግራይ ተወላጅ በመሆኑ
- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ክልሉ የሚገባው የእርዳታ መጠን ከፍ ያለ ቢሆን በቂ አይደለም እየተባለ መሆኑ
- በክልሉ እርዳታ የማድረስ ሥራ ላይ ያሉት አካላትም ከፈተኛው እትረጥ የነዳጅ እንደሆነ መግለጻቸው
ሊንክ – https://apnews.com/article/africa-united-nations-kenya-ethiopia-world-health-organization-9
The Guardian
- የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም በትግራይ ቀውስ የዓለማቀፍን ማህበረሠብ ግድየለሽነት ጥቁር በመሆን የመጣ እንደሆነ መናጋሩን ነው ያብራራው።
የተነሱነጥቦች
- ቴድሮስ የትግራይ ችግር በራሡ በኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመ እንደሆነ መናገሩ
- ዶክተሩ በዚህ ዓለም ላይ ያልታየና እሰቃቂ ጭካኔ በመንግስት የትግራይ ህዝብ ላይ ተፈጽሟል ማለቱ
- ዶክተሩ የጋዜጠኞችን መከልከልም በማንሳት መንግስትን መውቀሳቸው
- ክልሉ ከበባ ውስጥ ነው ያለው የሚለውን ክሥ አሁን ማንሳቱን
- የዓለማቀፍ ማህበረሠብ ጥቁር በመሆናቸው ትኩረት እንደነፈገው መውቀሱ
ሊንክ- https://www.theguardian.com/world/2022/aug/18/tigray-