የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
VOA
ኢትዮጵያ የእርዳታ ድርጅቶች በአሽከርካሪዎች ያልተፈቀደ ነዳጅና መሳሪያ ወደ ትግራይ እያስገቡ ነው ስትል መክሰሷን የሚተርክ ነው።
- በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ዕርዳታ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት የእርዳታ መኪናዎች የተከለከሉ ምርቶችን በድብቅ እንዳያስገቡ ቁጥጥር እያድረገ እንደሆነ በመግለጽ ጉዳዩን በትኩረት የሚያየው እንደሆነ ለማሳየትና መንግስት አሁንም እርዳታን ለመከልከል አዝማምያ ያለው እንደሆነ ለማሳየት ያለመ ነው።
- የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኤጀንሲ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ “የነግድ መርከቦች አሽከርካሪዎች እንደ ተጨማሪ ነዳጅ በርሜል፣ የሳተላይት ስልኮች እና ሌሎች ቁሳቁሶች ለአሸባሪው ህወሓት ለመውሰድ ሙከራ እያድረጉ መሆናችውን ገልጾ ያን መንግስት ፈጽሞ እንደማይፈቅድ ማሳወቁንም ለመግለጽ ሞክሯል።
- ዕርዳታ ለመስጠት ነው በሚል የእርዳታ ሰጪዎች ነን የሚሉ ከተፈቀደላቸው ምግብ ነክ እርዳታ በስተቀር ሌላ የጦር መሳሪያዎችን ይዘው ወደ ሀገራችን እንደሚገቡ በመጠርጠሩ የኢትዮጵያ የእርዳታ ሰጪዎች ላይ ክስ መመስረቱንም ነው የጻፈው።
- ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ
ሊንክ https://www.voanews.com/a/ethiopia-accuses-drivers-of-delivering-unapproved-fuel-equipment-to-tigray-/6605371.html
All Africa
ዚምባብዌ ያለው የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ መንግስቱ ኃ/ማርያም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ፍንጭ ሰጥተው ፍትህ እንዲጠየቁ የሚል ጥያቄ እያነሳች ቢሆንም ተቺዎች ግን እየገዙት እንዳልሆነ ዘገባው።
- ይህ የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍሬድሪክ ሻቫ የተደናቀፈ ይመስላል። ለአሜሪካ ድምጽ (ቪኦኤ) እንደተናገሩት “የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ ዚምባብዌ መንግስት ከቀረበ ለጥያቄው ምላሽ በዚምባብዌ መንግስት በኩል ከኢትዮጵያ መንግስት ለቀረበለት ህጋዊ ጥያቄ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል” ማለታቸውን እንደገለፁ ዘገባው ገልፆል።
- ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ
ሊንክ – https://allafrica.com/stories/202206070002.html
CGTN
- በኢትዮጵያ በነበረው ግጭት ተጎጂዎች እየተረሱ እንደሆነ ለማሳየት የሚዘግብ ዘገባ ነው ።
- ፍሰሓ አዱኛ በተባለ ግለሠብ የተጻፈ ጽሁፍ ነው ።
- አሁን ግጭት የለም ቢባልም ነገር ግን ተመልሶ የመባባስ ስጋት እየፈጠረ እንደሆነም የገለጸ ዘገባ ነው።
- በየአማራ እና አፋር ክልል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁን ችግር ላይ እያሉ የተረሱ በመሆናቸው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊዘነጋ እንደማይገባ ለማሳሰብ የሞከረ ትንተና ነው።
- ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ