የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሐምሌ 25፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 1 |2022
Daily News Egypt
- የግብፅ ኤክስፐርት ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ የምትሞላው የአባይ ግድብ ሙሌት የዓለም አቀፍ ህግን እንደጣሰ መክሰሱን የሚዘግብ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- ኢትዮጵያ በሐምሌ ወር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ማጠራቀሚያ ሶስተኛው ምዕራፍ የመሙላት ስራ እንደምትቀጥል ለግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፃፈችው ደብዳቤ ኢትዮጵያ መጻፏ
- የግብጽ መንግስት የህዳሴ ግድብን ሦሰኛ ሙሌትን እንደምትቃወም የሚገልጽ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ደብዳቤ መላኩ
- ግብፅ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መመለሷ
Menafn
- ኢትዮጵያ በሱማሌ ክልል ውስጥ የመከለከያ ቀጠና ልትፈጥር መሆኑ ነው የተጻፈው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ታጣቂውን አልሸባብን ለመዋጋት በሶማሊያ ድንበር ላይ የመከላከያ ቀጠና ለመፍጠር ያቀደውን እቅድ በደስታ መቀበላቸው
- ይህ ጉዳይ የበለጠ ውጥረት ሊፈጥር እንደሚችል የደህንነት ተንታኞች ማስጠንቀቃቸው
- ባለፈው ሳምንት የአልሸባብ ታጣቂዎች ከበርካታ አቅጣጫዎች ወደ ክልሉ ቢገቡም ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸውና የጸጥታ ሃይሎችም ቀሪዎቻቸውን በማፈላለግ ላይ መሆናቸው
- የመጀመሪያው ምዕራፍ መጠናቀቁን ተገልጾ ኢትዮጵያ በልሸባብ አሸባሪ ቡድን ላይ አሁንም ልትወስድ ስላቀደችው ቀጣይ እርምጃም ማሳወቃቸውን ነው ።
- ሁለተኛው ምዕራፍ በሶማሊያ ውስጥ ከአሸባሪዎች የፀዳ የጸጥታ መከላከያ ቀጠና መፍጠር እንድሆነ መነገሩ
ሊንክ https://menafn.com/1104622411/Ethiopia-To-Create-Buffer-Zone-Inside-Somalia-Proper