የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሐምሌ 19፣ | 2014 ዓ.ም – July 26 |2022
The Africa report
- በመንግስት እና በህወሐት መካካል ባለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁለቱም ወገኖች ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን በማመልከት ጥንቃቄ የተሞላበት ብሩህ ተስፋ እንዳለው የሚዘግብ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- ከታህሳስ ወር መገባደጃ ጀምሮ በፌዴራል መንግስት እና በህወሐት መካከል ትልቅ ግጭት ያልተደረገ ሲሆን በመጋቢት 24 በፌዴራል መንግስት የታወጀው የአንድ ወገን ሰብአዊ ተኩስ አቁም በአብዛኛው መጽናቱን ።
- በሚያዝያ ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ ህወሓት በአፋር ክልል ከያዘው ግዛት ለቆ መውጣቱ
- የፊደራል መንግስት የእርዳታ ጭኝ ተሸክርካሪዎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ ማመቻቸቱን
ሊንክ https://www.theafricareport.com/226317/ethiopia-an-end-in-sight-to-the-tigray-conflict/
Anadolu Agency
- የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ የአባይን ግድብ በተመለከተ ኢትዮጵያ የምትወስደውን እርምጃ ያልተገባ ውጤት ያመጣል በሚል አስጠነቀቁ ይላል።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባውን አወዛጋቢ የሆነ የግድብ ፕሮጀክትን አስመልክቶ ለአስርት አመታት በዘለቀው ውዝግብ ውስጥ ኢትዮጵያ የምትወስደው እርምጃ የሚያስከትለውን ውጤት ሁሌም እንደተለመደው ማስጠንቀቃቸው።
- በግብፅ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አል ሲሲ ከሶማሊያ አቻቸው ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙርያ እንደተነጋገሩና ያም የኢትዮጵያ እርምጃ የአንድ ወገን እርምጃ ነው በሚልና በዚያ ዙርያ ያላቸውን አቋም የተጋሩበ እንደሆነ
- አል ሲሲ ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ጋር ያደረጉት ውይይት በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ለውጦች ላይ የተመሰረተ መሆኑ
- “በዚህ አስፈላጊ እና ስትራቴጂካዊ ክልል ውስጥ ደህንነትን እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ በጋራ ለመስራት ተስማምተናል” ማለታቸው።
- የግብፅ መሪ ከሶማሊያ አቻቸው ጋር በቀይ ባህር የፀጥታ ጉዳይ ላይ በግብፅ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው
- ግብፅ እና ሱዳን ሁለት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በአባይ ግድብ አሞላል እና አሰራር ላይ ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንደሚፈልጉና ይህም ጥያቄ ደግሞ በኢትዮጵያ ተቃውሞ እንደቀረበበት