የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
መሰከረም 20 / 2017 ዓ.ም Sep 30 /2024
Atalayar
በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል እየጨመረ የመጣው ውጥረት ከግብፅ ጋር ተቀላቅላ የአፍሪካ ቀንድን አደጋ ላይ መጣሉን ስለመናገሩ
ዋና ዋና ነጥቦች
- ውጥረቱ እየጨመረ፡ ኢትዮጵያ በሶማሌ ላንድ የባህር ዳርቻን ለመከራየት ማቀዷ ሶማሊያን አስቆጥቶ ቀጠናዊ ውጥረቱ እንዲባባስ አድርጓል።
- የግብፅ-ሶማሊያ ወታደራዊ ስምምነት፡ ሶማሊያ ከግብፅ ጋር ወታደራዊ ስምምነት በመመሥረቷ የጦር መሣሪያ ጭነት እንዲጨምር አድርጓል።
- የአልሸባብ ስጋት፡ በሶማሊያ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ደካማ በሆነበት ወቅት አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች ለአልሸባብ ታጣቂዎች ኃይል ሊሰጡ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ።
- የኢትዮጵያ ወታደሮች ስጋት፡ ሶማሊያ በአፍሪካ ኅብረት አልሸባብን በመዋጋት የተሳተፉትን የኢትዮጵያ ወታደሮችን እንደምታስወጣ ዝታለች።
- ሊከሰት የሚችል አለመረጋጋት፡ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለው ትብብር መበላሸት አልሸባብን ለመጠቀም የጸጥታ ክፍተቶችን ሊፈጥር ይችላል።
- የቆሙ የሽምግልና ጥረቶች፡ ቱርክና ሌሎች የውጭ ኃይሎች ለሽምግልና ያደረጉት ሙከራ ውጤት አላመጣም።
- የጦር መሳሪያ አቅርቦት ውንጀላ፡ ሶማሊያ ኢትዮጵያ ለፑንትላንድ የጦር መሳሪያ ታቀርባለች ስትል ከሰሰች፣ ይህም ግንኙነቱን የበለጠ እያሻከረ ነው።
Garowe online
ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ውጥረት የዓባይን ውሃ እና የሶማሊያን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳየቷን እና ኢትዮጵያ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአንድ ወገን /በኢትዮጵያ/ ውሳኔ መስራት የአለም አቀፍ ህግጋትን እንደጣሰች ፅሁፉ ግብፅ መክሰሷ የሚያብራራ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- ግብፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በተነሳ ግጭት የአባይን ውሃ ለመጠበቅ ቃል ገባች።
- የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢትዮጵያ የግድቡን ፕሮጀክት በአንድ ወገን በመጀመር አለም አቀፍ ህግን እየጣሰች ነው ሲሉ ከሰዋል።
- ግብፅ የእስራኤልን የጋዛ ድርጊት በማውገዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቃለች።
- ግብፅ ግጭቱን ለመፍታት በሽምግልና ላይ ስትሆን ሶማሊያን ከኢትዮጵያ ስጋት ለመጠበቅ ቆርጣለች።
ሊንክ https://www.garoweonline.com/en/news/somalia/egypt-vows-to-defend-nile-waters-and-somalia-s-sovereignty-amid-escalating-tensions-with-ethiopia
Ahram
ግብፅ ለሶማሊያ የምትሰጠው ድጋፍ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት እና ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውዝግብ ላይ ያላት አቋም መግለጻን በማንሳት የግብጹ መሪ ፕሬዝደንት ኤል ሲሲ ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የውሃ መብት ለማስጠበቅ ውይይት ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ከፍ እንዳለ ስመለግለጻቸው የሚተንትን ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- ግብፅ እሁን እያደረገች ያለች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ውጥረት የተነሳ ለሶማሊያ መረጋጋት እና ሉዓላዊነት የምትሰጠው ድጋፍ መሆኑን።
- በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውዝግብ ዙርያ የግብፅ አቋም በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የውሃ መብት ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት አጽንኦት ስለመስጠቷ
- የግብፅ የውሃ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች ላይ የምታደርገው መዋዕለ ንዋይ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በውሃ አያያዝ ላይ ለመጠቀም ያላትን ቁርጠኝነት መግለጻቸው
ሊንክ https://english.ahram.org.eg/News/532686.aspx