የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
26 | January 5. 2024
HORN OBSERVER
የመረጃው እንድምታ
በሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰውና ታጣቂ ሆኖ ከሶማሊያ መንግስት ጋራ በታቀራኒ የተሰለፈውን አልሸባብን አዲስ መግለጫ ይዞ የወጣበት ሲሆን በመግለጫው አልሸባብ ሀላፊ ነው ያለውን ግለሰብ ጠቅሶ በቅርቡ ከሶማሊያ ላይ arms embargo በየተባበሩት መንግስታት ምክርቤት lift የሚደረግ ከሆነ አዳደስ መሳሪያዎችን ለመታጠቅ እንዳቀዱ በመግለጫው የተካተተ መሆኑን ይጠቁማል፨ በዚህም አሸባሪ ቡድኑ አዳዲስ ምልምሎቹን ያስመረቀ ሲሆን ኢትዯጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈረመችውን የወደብ ስምምነት ከሶማሊያ መንግስት ጋራ የአቋም ልዩነት እንደሌለውና ለዉጊያም እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ማስተላለፉ የሚገልጽ ነው።
NATION
የመረጃው እንድምታ
የኢትዯጵያ እና የሶማሊላንድን የወደብ ሊዝ ስምምነት ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት የአቋም መግለጫ ያወጡ ሲሆን AFP ያጠናቀረውን መረጃ ያወጣው Nation ከኢትዯጵያ አቋም በተቃራኒ የተሰለፉ ሀገራትን መግለጫ ሲሆን ስምምነቱን ካለመደገፋቸውም በላይ እንግሊዝን ጨምሮ በቀጠናው ያለውን ውጥረት እንዳሳሰባቸው መግለጫ ያወጡ ሀገራትን አቋም ይዞ ወጥቷል፨ በዚህም ኢንግሊዝ ለሶማሊያ ያላትን ድጋፍ እንደምሳሌ በመግለፅ፥ ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባቸው በሶማሊያ በኩል ጥሪ መቅረቡን የሚያስረዳ ነው።
ሊንክ ፦ https://nation.africa/africa/news/uk-urges-restraint-over-ethiopia-somaliland-deal–4482698
POST ONLINE MEDIA
የመረጃው እንድምታ
የኢትዯጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ 94 በመቶ የሚሆነውን ያህል መጠናቀቁን በኢትዯጰዕያ መንግስት በኩል ይፋ መደረጉን የሚያመላከት መረጃ ነው።
ሊንክ፦ https://www.poandpo.com/news/ethiopia-completes-94-of-grand-renaissance-dam/