የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጥቅምት 29 | nov 9, 2023
Africa news
የመረጃው እንድምታ
የኢትዮጵያ ጦር የላሊበላ ከተማ ከዚህ በፊት ተቆጣጥሯት የብነበርቸውን የፋኖ ሚሊሻዎች ቅድስቲቱን ከተማ ለቀው ከወጡ በኋላ እንደገና መቆጣጠር እንደቻሉ የሚያብራራ ነው።
BBC
የመረጃው እንደምታ
መረጃው የኢትዮጵያን የባህር በር የመጠቀም አጀንዳ ጉዳይን ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያን ወደብ ተጠቃሚ ለማድረግ ያደረጉትን ጥረት እና ለዚህ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ክርክሮች ቢኖሩትም የሃይል ስጋት በተለይም የኢትዮጵያን የውስጥ ግጭቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት ስጋት እንደሚፈጥሩ ያለውን አንድምታ ያብራራል።
ሊንክ – https://www.bbc.com/news/world-africa-67361386
FIRST POST
የመረጃው እንደምታ
የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በታንዛኒያ በትልቅነቱ እና በህዝብ ብዛት በኦሮሚያ ክልል ለአምስት አመታት የዘለቀውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም አዲስ ውይይት እያደረጉ እንደሆነ በማንሳት ውይይቱ ለአስር ቀናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች የወደፊት ስምምነት ላይ ብሩህ ተስፋ እንዳላቸው የሚገልጽ ነው።
ሊንክ – https://www.firstpost.com/opinion/vantage-is-ethiopias-nobel-laureate-president-stoking-another-war-13369102.html