የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ጥቅምት 19 | oct 30, 2023
Government of Ireland
የመረጃው እንድምታ
የአየርላንድ ሚኒስትር ሼን ፍሌሚንግ ኢትዮጵያን እና ዩጋንዳን ሊጎበኙ እንደሆነ እና በሁለቱም ሀገራት ያለውን የሴቶች ላይ ያለውን ተእጽእኖ ለመቀየር እና ሁለቱን ሀገራት በንግድ በልማት ትብብር እና በባህል ልውውጥ ላይ ጠቃሚ ሚናዎችን ለመለዋወጥ እንደሚገኙ የሚያሳይ መሆኑን እና በተጨማሪም ከአየርላንድ ሚስዮናውያን ጋርም እንደሚገናኙ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።
ሊንክ https://www.gov.ie/en/press-release/5501f-minister-sean-fleming-to-visit-ethiopia-and-uganda/
The Libya Observer
የመረጃው እንድምታ
ሊቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እና ከአፍሪካ ገበያ ጋር ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን የትብብር ስራ ላይ መወያየታቸውን እና ስምምነቱ በእጥፍ ግብር በመክፈል ሥራን በመቆጣጠር እና በሁለቱም ሀገራት ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በሚቻልበት መንገድ ላይ መከራከራቸውን የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።
ሊንክ https://libyaobserver.ly/economy/libya-ethiopia-discuss-cooperation-trade-and-investment
Anadolu Ajansı
የመረጃው እንድምታ
የቱርክ ሪፐብሊክ 100ኛ የምስረታ በአል በሚያከብር ሰአት የኢትዮጵያ መንግስት የብልጽግና እና ሰላም ወደፊት ባለው ጊዜ እንደምትመኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መናገሩን እና የኢትዮጵያ መንግስት እና የቱርክ መንግስት ጠንካራ አጋርነት እና ዘላቂ ወዳጅነት እንዳላቸው የሚያሳይ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።
African Development Bank
የመረጃው እንድምታ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ኃላፊ ለባለሀብቶች በአለም የምግብ ሽልማት ላይ እንድተወያዩት ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በስንዴ ምርት ራሷን ችላ ለጎረቤቶቿ ሀገራት ስንዴ መላክ እንደጀመረች እና ይህ ደግሞ የሚበረታታ እንደሆነ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።