የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ጥቅምት 18 -2016 | Oct 29, 2023
Ahram Online
የመረጃው እንድምታ
ኢትዮጵያ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በአንድ ወገን መስራቷ ከ100 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የግብፅ ህዝቦች “የህልውና ስጋት” ተደርጎ መወሰዱን የውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ሰዊላም ተናግረዋል።
ሊንክ – https://english.ahram.org.eg/Category/1/1234/Egypt/Sisi,-Guterres-exchange-views-on-latest-.aspx
AIRSPACE REVIEW
የመረጃው እንድምታ
አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገው ወታደራዊ ትርኢት በሩሲያ የተሰሩ ክራሱካ-4 የኤሌክትሮኒክስ የጦር መሳሪያዎችን እንዳሳየ እና ክራሱካ-4 በዝቅተኛ የምድር ምህዋር ላይ ያሉ ሰላይ ሳተላይቶችን፣ በመሬት ላይ የተመሰረተ ራዳር እና አየር ወለድ ራዳርን ጨምሮ የተለያዩ ስጋቶችን የሚያስወግድ ሁለገብ ሴሉላር ሲስተም ያላቸው መሳርያዎች እንዳላት ማሳየቷን እና መሳእያዎቹም ሩሲያ ሰራሽ መሆናቸውን ገልጿል።
INDEPENDENT
የመረጃው እንድምታ
የአሜሪካ የንግድ ማለስልጣናት አሜሪካ በአፍሪካ ላይ ያላትን ፖለቲካ ተጽዕኖን ለመጨመር ኢትዮጵያ የታገደችበት የAGOA ፕሮግራም ላይ ለውጦች መደረግ እንዳለባቸው እና አንዳንድ የአፍሪካ መንግስታት እና የኢንዱስትሪ ቡድኖች የንግድ እና አዲስ ባለሀብቶች በአጎአ የወደፊት ሁኔታ ላይ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ለውጦች ሳይደረጉ ለ 10 ዓመታት የቆዩ በመሆናቸው ማሻሻያ ሊደርግለት እንደሚገባ ባለስልጣናቱ ያቀረቡትን የማሻሻያ ሀሳብ የሚተነትን ነው።
ሊንክ – https://independent.ng/agoa-programme-needs-changes-u-s-trade-official/