የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ጥቅምት 15 -2016 | Oct 26, 2023
Reuters
የመረጃው እንድምታ
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የባህር ወደብ መዳረሻን ለማስጠበቅ ሃይል ሊጠቀሙ ይችላሉ በሚል የጎረቤት ሀገራትን ስጋት ለማርገብ ዛሬ የመከላከያ ቀን መርሀብግር ላይ የተናገሩት ንግግር ላይ ያተኮረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትኛውንም ሀገር እንደማይወር እና ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ቀይ ባህር የመጠቀም መብቷን ማስከበር እንዳለባትን መግለጻቸውን የሚያብራራ ነው። ጉዳዩ በቀጠናው አዲስ የግጭት መንሳኤ ሊሆን እንደሚችል የጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራን ምላሾችን በማካተት የሚያብራራ ነው።
ሊንክ – https://www.reuters.com/world/africa/ethiopia-pm-abiy-seeks-quell-neighbours-concerns-over
ISS AFRICA
የመረጃው እንድምታ
“ጦርነት ከማቆም ባለፈ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ሰላም ያስፈልጋታል በሚል ” ከ ISS አፍሪካ በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት እና አጠቃላይ የሰላም ስምምነት አስፈላጊነት እና የግጭቱን ውስብስብነት እና የረዥም ጊዜ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ እጉልቶ ያሳያል። በተጨማሪም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሰላሙ ሂደት ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ እና የተገለሉ ቡድኖችን ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን እንደሆነ በአጽዕኖት በማንሳት ኢትዮጵያ በስላም ግንባታ ስራው ወደፊት እንድትራመድ እና መረጋጋትን ለማስፈን ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝባል።
ሊንክ – https://issafrica.org/iss-today/beyond-a-cessation-of-hostilities-ethiopia-needs-comprehensive-peace
ISS AFRICA
የመረጃው እንድምታ
የኢትዮጵያን ግድብ ሥራ ለማስኬድ ‹ሕጋዊ› ስምምነት ላይ ለመድረስ በሦስቱ አገሮች መካከል በታህሳስ ወር አዲስ ድርድር በአዲስ አበባ እንደሚጀመር በመጥቀስ ውይይቱ በሶስቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ያለመ ሲሆን ባለሙያዎች ይህኛው ድርድር አራተኛው ዙር እንደሆነ እና ስምምነት ላይ ለመድረስ “የመጨረሻው ዕድል” እንደሆነ የገለጹ መሆኑን የሚያብራራ ነው።
ሊንክ – https://english.aawsat.com/arab-world/4629066-round-4-gerd-talks-what-are-possible-scenarios