የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ጥቅምት 6 -2016 | Oct 17, 2023
Africa News
የመረጃው እንድምታ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለሦስተኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር ፎረም በቤጂንግ ጉብኝታቸው ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በኢኮኖሚና ንግድን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን ለማስፋት ባላቸው ፍላጎት መሰረት በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ስር ያሉትን ጨምሮ የሁለትዮሽ የትብብር ሰነዶች መፈረማቸውን ይገልጻል። ይህ ተነሳሽነት ቻይና የጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖዋን ለማስፋፋት እንደ መሳሪያ እንደምትጠቀም አድርገው እንደሚቆጥሩትም የሚያብራራ መረጃ ነው።
CGTN
የመረጃው እንድምታ
ቻይና እና ኢትዮጵያ የጋራ ልማትና ትብብርን ለማሳደግ ሁለንተናዊ የአየር ሁኔታ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመመስረት ከፍተኛ ጥራት ባለው ልማት ላይ ትብብርን ለማጠናከር እና ዋና ጥቅሞቻቸውን እና ዋና ጉዳዮችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ እርስ በርስ ለመደጋገፍ እንዲሁም በሰላም አብሮ የመኖር እና የመማማር ቁርጠኝነት እንዳላቸውም እንደገለጽ የሚያብራራ ነው።
BNN Bloomberg
የመረጃው እንድምታ
የኢትዮጱያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በኤርትራ ወደብ በኩል ቀይ ባህርን ለማግኘት ያደረጉት ግፊት በኤርትራ መንግስት አሉታዊ ምላሽን በመሰጠቱ የግጭት ስጋትን ከፍ እንዳደረግው በመግለጽ የኢትዮጵያ ለሀሳቡ ስኬት መንግስት ለድርድርም ሆነ ለጦርነትም የሚበቃ በቂ አቅም እንዳላጎለበተ የሚተነትን ነው።
ሊንክ – https://www.bnnbloomberg.ca/ethiopia-says-lack-of-port-access-can-fuel-future-conflict-1.1985611