የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጥቅምት 3| oct 14, 2023
UN News
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ምርምራ ኤክስፐርቶች ኮሚሽን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጉዳይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ጊዜ በማጠናቀቁ በመብት ጥሰቶቹ ተጎጂ የሆኑ ዜጎችን ያለፍትህ እንደሚያሰቀር የሚገልጽ ሲሆን የተጎጂዎችን ፍትህ የማግኘት እድል ለማስፋት የኮሚሽኑ ተልዕኮ መቀጠል እንዳለበት የሚያብራራ ነው።
ሊንክ https://news.un.org/en/story/2023/10/1142297
Reuters
የመረጃው እንድምታ
የኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ በመቆየቷ ከቻይና የብድር ገንዘብ ክፍያ የእፎይታ ጊዜ እንዲራዘምላት እንደተደረገው ሁሉ ከሌሎችም አበዳሪዎች የብድር ገንዘብ እዳ ክፍያ ጊዜ እንዲራዘምላት እንደምትፈልግ የMF ሀላፊ ማስገንዘባቸውን ያብራራል።
ሊንክ www.reuters.com/world/africa/ethiopia-getting-debt-relief-china-asking-others-similar-imf-
Newswire com
የመረጃው እንድምታ
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን አንገብጋቢ ቀውስ እና ሰፊ አንድምታውን ለመቅረፍ ኮንግረንስ በማዘጋጀት በሀግሪቷ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የገለጻ እና ውይይቶች ለማካሄድ ማክሰኞ – ኦክቶበር 17 ቀጠሮ መያዙ ያመልክታል። በገለጻው ሪቻርድ ጋዛል – የDefense of Christians ድርጅት ዋና ዳይሬክተር እና አቶ መስፍን ተገኑ- የአሜሪካ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ፣ የመኢአድ መሪዎች እና ኢትዮጵያውያን አሜሪካዊያን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፡- ቤቲ ተከስተ፣ ዋሲ ተስፋ፣ ትግስት እንግዳው፣ ጀማል ካቴስ፣ የመሳሰሉ እንደሚገኙበት የተገለጽ ነው።
ሊንክ https://www.newswire.com/news/american-ethiopian-public-affairs-committee-aepac-to-host-