የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሐምሌ 8፣ | 2014 ዓ.ም – July 15 |2022
Reuters
የዓለማቀፍ የገንዘብ ተቋም IMF ኢትዮጵያን ጨምሮ የ3 ህገራት የብድር እዳን ጉዳይ መልሠው እንድመለከቱት ጥሪ ማቅረቡን ነው የጻፈው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
ለሀገራቱ እዳቸውን ማራዘም ወይም መሠረዝ ሌሎች የትብብር ዳጋፎችንና በተእያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ድጋፍ ለሚሹ እነዚህ ተበዳሪ ሀገራት መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር እንደሆነ።
በኢትዮጵያም የጦርነቱ ጫና የሀገሪቷን የብድር መክፈያ አቅምና ሁኔታን አስቸጋሪ ያደረገው ቢሆንም ይህ ነው ተብሎ የማይገለጽ አስቸጋሪ ሁኔታ በመፍጠሩ እርምጃው እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተቋሙ መግለጹ።
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጭኑ
The East African
- የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የኬኒያን ምርጫን ለመታዘብ ወደዝያ የሚያቀኑትን የኢጋድ ታዛቢዎችን ሊመሩ ኬኒያ መግባታቸውን በአዉንታዊ መልኩ የሚዘግብ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የመንግስታቱ ድርጅት የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በመጪው የኬንያ አጠቃላይ ምርጫ የታዛቢ ተልዕኮውን እንዲመሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መሾማቸው
- ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ስምንት ሀገራትን ያቀፈው ኢጋድ፣ ግብዣውን የኬንያን የዴሞክራሲ ሂደት ለማራመድ እንደ ክብር እንደሚወስድ መናገሩን ዘገባው ተንትኖል።
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጭኑ