የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም 21| Oct 2, 2023
Travel Daily News
- የዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር አዲስ የአቅም ማጎልበቻ እና የማስፈጸሚያ ድጋፍ ስምምነትን ማድረጉን የሚገልጽ ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- አዲስ ስምምነት አለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ዋና ፀሃፊ ሁዋን ካርሎስ ሳላዛር እና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ጌታቸው መንግስቴ እንደተፈራረሙ
- ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ደረጃዎች እና ልማዶችአተገባበርን በማሳደግ ለግዛቱ የአቪዬሽን ዘርፍ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ እና ዘላቂ ልማትን የሚያግዝ አዲስ የማስፈጸሚያ ድጋፍ ስምምነትን ከ አለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ጋር ስምምነት እንዳደረገች
- ስምምነቱ በጣቃለይ አሁን ላይ አለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቢሮ ከሚሰጠው የትግበራ ድጋፍ አገልግሎት ጋር በተጣጣመ መልኩ የልምድ ልውውጥን፣ የፕሮጀክት አስተዳደርን፣ የስልጠና ፓኬጆችን አቅርቦትና ከግዥ ጋር የተገናኘ የትግበራ ድጋፍ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን አቅርቦትን እንደሚያጠቃልል የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።
Bloomberg
- በአለም ጤና ድርጅት ኃላፊ በቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ የተደረገ ሚስጥራዊ ሴራ የሚያሳይ ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ መንግስት በቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ ላይ ያደረገውን ምርመራ የሚያሳይ የሰነድ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሆነ
- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ ሆነው ያገለገሉት የሀገራቸው ልጅ ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ሜስጥራዊ ስለላ እንደተደረገባቸው
- በሌላ በኩል የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ የሆኑት ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁን ላይ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ለመሄድ ዋስትና ሳይሰጣቸው ለመመለስ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ማሳወቁን የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ።