የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሰኔ 23 | 2014 ዓ.ም – June 30 |2022
VOA
- የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በሰላማዊ ድርድር ጉዳይ ዙርያ ውዝግብ ውስጥ የመግባታቸው ሚስጥር የህወሓት ድርድሩን ያለመፈለግ ሊሆን እንደሚችል የሚተነትን ዘገባ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር ያለውን ግጭት ለመቋጨት የትኛውንም የድርድር አማራጭ በመጠቀምና በአፍሪካ ህብረትም አደራዳሪነት እድኒደረግ እንደሚፈልግ
- ነገር ግን ህወሐት በአፍሪካ ህብረት ላይ እምነት እንደሌለው በመግለጽ ኬንያ እንድታስታርቅ እንደሚፈልግ
- በሁለቱ ወገኖች ተቃራኒ ፍላጎቶች መንጸባረቅ የተነሳ የድርድሩ መሳካት አጠራጣሪ እንደሚያደርገው።
- ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጭኑ
Africa news
- የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ውጥረቱ እየተባባሰ መምጣቱን እንዳሳሰበው የገለጸውን የሚተነትን ዘገባ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መሪ ሙሳ ፋኪ ማሃማት ሱዳን እና ኢትዮጵያ ከወታደራዊ ፍጥጫ እንዲቆጠቡ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የድንበር ግጭት በድርድር እንዲያደርጉ መጠየቃቸው
- የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፤ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል የተፈጠረውን ወታደራዊ ውጥረት ህብረቱ በቅርበት እየተከታተለው እንደሆነ
- አፍሪካ ህብረት ባወጣው መግለጫ ላይ ኢትዮጵያ እና ሱዳን “የተፈጠረውን ውጥረት ከሚያባበስ ማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ እንዲታቀቡ” ማሳሰቡን ከተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ማካከል ናቸው።
- ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጭኑ