Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read
                                                                                                                                                                        ነሃሴ 23AUG 29, 2023

Al Jazeera

 • ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ትደራደር ይሆን የሚል የቪዲዮ ዘገባ ነው ።

    የተነሱ ነጥቦች

 • አዲስ አበባ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ሌላ ስብሰባ በመደረጉ ግድቡ ጎረቤቶቿን እንደማይጎዳ እንደተናረገች
 • ኢትዮጵያ በሰማያዊ አባይ ላይ በምትገነባው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚገመት የሃይል ማመንጫ ግድብን አስመልክቶ ለዓመታት የዘለቀውን አለመግባባት ለመፍታት ተስፋ  ማድረጋቸውን
 • ግብፅ እና ሱዳን ግድቡን ለማስኬድ ህጋዊ የሆነ ስምምነት እንፈልጋለን ሲሉ ኢትዮጵያ በበኩሏ የትኛውም ስምምነት መካሪ መሆን አለበት  እንዳለች
 • ሁለቱም ሀገራት ግድቡን ለወሳኝ የውሃ አቅርቦታቸው ስጋት አድርገው ሲመለከቱት ኢትዮጵያ ግን ለልማት እና የኤሌክትሪክ ምርቷን በእጥፍ ለማሳደግ አስፈላጊ ነው ብላ  እንደወሰደች
 • የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በውሃ ተቋማት፣ በእርሻ መሬት እና በአጠቃላይ የአባይ ውሃ አቅርቦት ላይ ሊደርስ ይችላል የሚል ስጋት  እንዳላቸው
 • በግብፅ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል በግድቡ ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ድርድር ለዓመታት ቆሞ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ሦስቱ ወገኖች ምንም አይነት ስምምነት ላይ አለመድረሳቸውን
 • ባለፈው ወር የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በካይሮ የሱዳን ጎረቤቶች የመሪዎች ጉባኤ ላይ ግድቡን መሙላት እና ማስኬጃ ህጎችን በተመለከተ ድርድር እንዲቀጥል መስማማታቸውን
 • የውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ሰዊላም ግድቡ መሙላት እና ማስኬጃ ደንቦች ላይ ሚዛናዊ እና ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት የሶስቱን ሀገራት ጥቅምና ፍላጎት የሚያረጋግጥ ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ መሆኑን   ማስመራቸውን
 • ግብፅ የሶስቱንም ሀገራት ፍላጎት የሚያሟሉ እና አስፈላጊው ሚዛናዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ በርካታ ቴክኒካዊ እና ህጋዊ መፍትሄዎች አሉ ብላ ታምናለች ማለታቸውን የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ    https://www.aljazeera.com/program/inside-story/2023/8/28/will-ethiopia-compromise-on-its-grand-renaissance-dam

 State Department

 • የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀመር ወደ ኬንያ እና ኢትዮጵያ መጎዛቸውን የሚገልጽ ነው ።

 የተነሱ ነጥቦች

 • የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ወደ ናይሮቢ እና ኢትዮጵያ  እንደሚጓዙ
 • ከኬንያ እና ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት እና ሌሎች አለም አቀፍ አጋሮች ጋር  እንደሚገናኙ
 • በሱዳን ስላለው ቀውስ እና ሁካታ ለማስቆም ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስፈን፣ ፍትህ እና ተጠያቂነትን ለመደገፍ በሚደረገው አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ጥረቶች ላይ እንደሚወያዩ
 • በኢትዮጵያ የጦርነት ማቆም ስምምነትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን በድርድር ለመፍታትም እንደሚወያዩ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ     https://www.state.gov/special-envoy-for-the-horn-of-africa-hammer-travels-to-kenya-and-ethiopia/

 Al monitor

 • ግብፅ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአባይ ወንዝ ግድብ ላይ ድርድር ቢቀጥሉም እንቅፋቶች አሁንም እንዳሉ የሚገልጽ ነው ።

 የተነሱ ነጥቦች

 • በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ድርድር ቀጥለዋል፣ ምንም እንኳን በዓባይ ወንዝ ሜጋ ግድብ ላይ የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረስ ባይቻልም እና በርካታ ፈተናዎች እንዳሉበት  እንደሚታወቅ
 • በሦስቱ ሀገራት መካከል የመጨረሻው ዙር ድርድር በካይሮ  መጀመሩን ነገር ግን ግብፅ ግድቡ እንዴት እንደሚሰራ እና እንደሚሞላ በሚደረገው ውይይት ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት  እንደምትፈልግ የግብፅ የመንግስት መረጃ አገልግሎት መግለጫ ማሳወቁን
 • ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት የጀመረችው በ2020 ክረምት ላይ  እንደሆነ
 • ኢትዮጵያ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ለዜጎቿ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማቅረብ ባለፈ በልማትና ድህነትን በመቅረፍ ረገድ እገዛ እንደሚያደርግ መናገሯን
 •  ኢትዮጵያውያን 44% ብቻ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን ከዩኤስ አለምአቀፍ ንግድ አስተዳደር የተገኘ መረጃ  እንደሚያሳይ
 • በሜጋ ግድቡ ላይ የተደረጉ ንግግሮች ከ10 ዓመታት በላይ ሲበሩ እና ሲጠፉ ቆይተዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከአፍሪካ ኅብረት (AU) እና ከሌሎችም የተደረገው ሽምግልና ስምምነት ላይ መድረስ  አለመቻሉን የአፍሪካ ህብረት ለመጨረሻ ጊዜ በግድቡ ላይ ቀጥተኛ ድርድርን በ2021 ማድረጉን
 • ኢትዮጵያ በመጋቢት ወር 90% የሚሆነው የግድቡ ግንባታ መጠናቀቁን እንዳስታወቀች እና  በሐምሌ ወር ኢትዮጵያ አራተኛውን የግድቡን ሙሌት የጀመረችው በዓመታዊው የዝናብ ወቅት እንደሆነ
 • ለኢትዮጵያም ከግድቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት መጀመሯን ባለፈው ዓመት ማስታወቆን
 • የአሁኑ ውይይት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው ወር በሱዳን ግጭት ላይ በካይሮ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ  እንደሆነ  ሁለቱ መሪዎች በግድቡ ላይ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ስምምነት ላይ ለመድረስ ቃል  ነመግባታቸውን
 • የግብፅ እና የሱዳን የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግን ኢትዮጵያ በአንድ ወገን ብቻ ግድቡን መሙላቷ በተለይም ድርቅ በሚከሰትበት ጊዜ በግዛታቸው የሚገኘውን የአባይ ወንዝ እና ገባር ወንዞቹን በአደገኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ እንደሚያምኑ
 • የናይል ወንዝ ለአካባቢው ሀገራት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ግብፅም ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን ውሃ ከወንዙ  እንደምታገኝ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ    https://www.al-monitor.com/originals/2023/08/egypt-ethiopia-and-sudan-resume-talks-nile-river-dam-obstacles-remain

France 24

 • በአማራ ክልል በተፈጠረ ግጭት ከ180 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ማስታወቁን የሚያሳይ ነው ። 

የተነሱ ነጥቦች

 • በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች ያለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ መባባሱ በጣም ያሳስበናል ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ማርታ ሁርታዶ በጄኔቫ ለጋዜጠኞች  መናገራቸውን
 • በአማራ ክልል በኢትዮጵያ ወታደሮች እና በክልሉ ፋኖ ሚሊሻዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት እና የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ሁኔታው ​​በእጅጉ  እንደተባባሰ
 • ከሀምሌ ወር ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 183 ሰዎች መሞታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ቢሮ ያሰባሰበው መረጃ  እንደሚያመለክት
 • በትግራይ አጎራባች አካባቢ የተካሄደው አውዳሚ ጦርነት ካበቃ በኋላ የአማራ ክልል ውጥረት መንገሱን
 • በሚያዝያ ወር የፌደራል መንግስት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የክልል ሃይሎችን እያፈራረሰ መሆኑን  ማስታወቁን
 • ይህ እርምጃ ክልላችንን ያዳክማል በሚሉ የአማራ ብሄርተኞች ተቃውሞ  ማስናሳቱን
 • በሀምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በብሄራዊ ጦር ሰራዊት እና ፋኖ በሚባሉ በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ የነበረ ሲሆን በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለስልጣናት 6 ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን
 • ሁኔታው ባለሥልጣናቱ ተጠርጣሪዎችን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመያዝ፣ የሰዓት እላፊ ገደቦችን የመጣል እና ህዝባዊ ስብሰባዎችን የመከልከል ሰፊ ስልጣን ይሰጣል ሲል ሃርታዶ  መናገሩን
 • በዚህ ህግ በመላው ኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ዘገባዎች መድረሳቸውን እና ከታሰሩት መካከል አብዛኞቹ የፋኖ ደጋፊዎች ተብለው የተጠረጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ወጣቶች መሆናቸው  እንደገለጸች
 • ባለሥልጣናቱ የጅምላ እስራት እንዲያቆሙ፣ የነፃነት መነፈግ በፍርድ ቤት እንዲታይ እና በዘፈቀደ የታሰሩትን እንዲፈቱ  እንደሚጠይቁ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ    https://www.france24.com/en/africa/20230829-more-than-180-killed-in-clashes-in-ethiopia-s-amhara-region-since-july-says-un

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *