የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሰኔ 18 | June 25, 2023
Xinhua
ኢትዮጵያ፣ የዕርዳታ አጋሮች የምግብ ዕርዳታን አላግባብ መመዝበሩን የሚያጣራ ኮሚቴ አቋቋመች የሚል ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ መንግስት እና የእርዳታ አጋሮች የጋራ ቴክኒካል ኮሚቴ በማዋቀር የምግብ ርዳታ አላግባብ መዘዋወሩን አንድ የኢትዮጵያ ባለስልጣን እንደገለጹ
- የኢትዮጵያ የመንግስት እንደ የተባበሩት መንግስታት የአለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ያሉ የእርዳታ አጋሮች እንዲታገዱ ያደረጋቸውን ህገ-ወጥ ድርጊቶች ኮሚቴው በጥልቀት እንደሚመረምር መግለጹ
- በኢትዮጵያ ብሄራዊ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የሚመራው ጥምር ቴክኒክ ኮሚቴ በእርዳታ ኤጀንሲዎች የምግብ ዕርዳታ እንዲቋረጥ ምክንያት የሆነውን ችግር ለመፍታት ግብአቶችን ለማቅረብ ከወዲሁ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገስት እንደገለጸ
- የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴው ስራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ የውይይት መድረኮችን ማካሄዱንም ዳይሬክተሩ መግለጻቸው።
- የ WFP መግለጫ ስማቸው ያልተጠቀሰ የሀገር ውስጥ እና የውጭ አካላት የጥላቻ እና የስም ማጥፋት መረጃዎችን እያሰራጩ ነው ሲል እንደከሰሰ የሚገልጹት ዋና ውና ነጥቦች ናቸው።
The New Arab
- በ2022 በኢትዮጵያ ያለውን ጨምሮ በጦርነት እና በተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ 71ሚ ሰዎች ሪከርድ ተገኘ የሚል መረጃ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የውስጥ መፈናቀል ሀገሮች በራሳቸው ድንበሮች ውስጥ ለመንቀሳቀስ የተገደዱ ሰዎችን የሚያመለክት እንደሆነና የውስጥ መፈናቀል ክትትል ማዕከል ሪፖርት ወደ ተለያዩ ሀገራት የሄዱትን ግምት ውስጥ እንዳላስገባ መግለጹ
- በዩክሬን፣ በሶሪያ፣ በኢትዮጵያ እና በሌሎችም አካባቢዎች አሁንም መፈናቀሎች እንደቀጠሉ እንደሆነ
- የሀገሮች ውስጥ መፈናቀል መከታተያ ማዕከል በ2022 ለሶስተኛ ተከታታይ አመት የቀጠለው የአየር ሁኔታ መለዋወጥ ክስተት ለአደጋም ለመፈናቀል ዋነኛ ምክንያት አድርጎ መጥቀሱን
- በዚህም በፓኪስታን፣ ናይጄሪያ እና ብራዚል የጎርፍ መፈናቀልን በማስመዝገብ በሶማሊያ፣ በኬንያ እና በኢትዮጵያ ለተመዘገበው አስከፊ ድርቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ማመላከቱን የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – http://www.milwaukeeindependent.com/newswire/report-finds-record-71m-people-internally-