Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ግንቦት  19 |  May 27, 2023

   CNN

  • የኤርትራ ሃይሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትግራይ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ተልዕኮ አስቁመዋል ሲሉ የእርዳታ ሰራተኞች ለሲኤንኤን ተናግረዋል።

የተነሱ ነጥቦች

  • የኤርትራ ሃይሎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚመራው የሰብአዊ ተልእኮ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል መንደር ውስጥ እንዳይገባ ባለፈው ሃሙስ እንደከለከሉ
  • ይህም በአካባቢው ያለው ጦርነትን ያስቆመውን የሰላም ስምምነት መጣሱን ነው ሲሉ በቦታው የነበሩ የእርዳታ ሰራተኞች ለ CNN ሚዲያ መግለጻቸው
  • ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የተሻሻለ የርዳታ ተድራሽነት ቢኖርም ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (UNOCHA) እንዲሁም የሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባለስልጣናት ግንቦት 25 ቀን 2023  ወደ ገምሃሎ መንደር እንዳይደርሱ በኤርትራ ጦር መከልከላቸውን የእርዳታ ሰራተኞች እንደገለጹ
  • “ከሸራሮ 16 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ዋዕላ-ንህቢ ከተጓዝን በኋላ ተልዕኮው እንደቆመ
  • የኤርትራ ጦር ከሸራሮ በቅርብ ርቀት ላይ በታህታይ-አዲያቦ ወረዳ (ወረዳ) አምስት ቀበሌዎችን (ሰፈሮችን) በመያዝ በትግራይ እንደሚገኝ መገለጹ
  • ባሉበት አካባቢም “ ዘረፋ፣ መሰረተ ልማቶችን ማፍረስ፣ መደፈር በኤርትራ ሀይሎች መቀጠሉ
  • ሲ ኤን ኤን ለጉዳዩ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መንግስታትን እንዳነጋገረ የሚገልጹት ዋና ነጥቦቹ ናቸው።

ሊንክ – https://edition.cnn.com/2023/05/26/africa/eritrean-forces-un-tigray-intl/index.html

 I24 NEWS

  • በኢትዮጵያ የትግራይ አማፂ ሃይሎች/ የህወሓት ታጣቂዎች እየፈረሱ ነው ይላል።

የተነሱ ነጥቦች

  • በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ትግራይ ክልል አማፂ ተዋጊዎች አርብ እለት ካሉበት አደረጃጀታቸው የፈረሱ እንደሆነና የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ አዲስ ተጨማሪ ደረጃ ላይ መድረሳቸው እንደተነገረ
  • በክልሉ የነብሩ “የትግራይ መከላከያ ሰራዊት” በሚል የተደራጁ ተዋጊዎች ወደ ተመረጡ ቦታዎች ማዛወር እንደሚጀምሩ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ስምምነቱን አፈፃፀም የሚቆጣጠረው መሆኑን እንደተገለጸ
  • የህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) የመጀመሪያው ዙር የቀድሞ ታጋዮችን መልሶ የማቋቋም እና የማቋቋም ፕሮግራም በይፋ እንደተጀመረ መገለጹ
  • በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የብሄራዊ መልሶ ማቋቋሚያ ኮሚሽን ምክትል ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያ የትግራይ ተወላጆች ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እንዲሰሩ ጥሩ ማቅረባቸው
  • ታጣቂዎች ይህን ሰላማዊ መንገድ በመጠቀም ህይወታችሁን በመቀየር በክልሉ ብሎም በኢትዮጵያ ልማት ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጭምር ጥሪ መቅረቡን የሚገልጹት ዋና ነጥቦቹ ናቸው።

ሊንክ  – https://www.i24news.tv/en/news/international/africa/1685126267-tigray-rebel-forces-

  All Africa

  • በኡጋንዳ ያሉ ኢትዮጵያውያን በ2023 የአፍሪካ ቀንን ከኡጋንዳዉያን ጋር ማክበራቸውን የሚገልጽ ነው።

የተነሱ ነጥቦች

  • የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኡጋንዳ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመሆን የአፍሪካ ቀን 2023ን ለማክበር በኮሎሎ የነጻነት ስፍራ ላይ ባደረገው ታላቅ ሰልፍ ላይ እንደተሳተፉ
  • የአፍሪካ ቀን ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት አመታዊ መታሰቢያ ሲሆን በአፍሪካ አህጉር በተለያዩ ሀገራት እንደሚከበር እና የዘንድሮው 60ኛ አመት የአፍሪካ ህብረት የምስረታ በዓል “የአፍሪካ ኢኮኖሚ ነፃነትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ
  • የበዓሉ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካምፓላ ፊልድ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በኮሎሎ የኢትዮጵያ የባህል አልባሳት እና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦችና መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዳከበሩ
  • በተጨማሪም በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የቡና ሥነ-ሥርዓት እና ባህላዊ ምግቦችን በማሳየት የኢትዮጵያን ባህልና ወግ በኩራት እንዳሳዩ
  • የኢትዮጵያ ዳስ የክብር እንግዳው የኡጋንዳዋ እንስት ጠቅላይ ሚኒስትር ሮቢና ናባንጃ በክር እንደተገኙ
  • ሌሎች ታዳሚዎችም እንደነበሩ ፣ የዲፕሎማቲክ ኮር ዲን፣ የኡጋንዳ እውቅና የተሰጣቸው የአፍሪካ ኤምባሲዎች ኃላፊ እና ተወካዮች፣ ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የወንድማማች ማህበራት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደተገኙ
  • ተሰብሳቢዎቹም ደስ የሚል ኢትዮጵያዊ “ጉርሻ ከአገልግል” ገለጻ እንደተደደረገላቸው  የሚገልጹት ዋና ነጥቦቹ ናቸው

ሊንክ  – https://allafrica.com/stories/202305260578.html

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *