Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

መጋቢት 14፣ | 2015 ዓ.ም – march 23  | 2023

Aljazeera

  • ኢትዮጵያ የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት የሰላም ማስፈን እቅድ አካል አድርጋ አቋቁማለች የሚል መረጃ ነው።

 የተነሱ ነጥቦች

  • የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለአፍሪካ ቀንድ ሰሜናዊ ክልል ሰአልም መስፈን አስተዋጻዎ የሚያደርገውን ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደመሰረቱጅ
  • ይህም ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስወገድና ለሰላም ስምምነቱ ትግበራ ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ
  • ውሳኔው በደቡብ አፍሪካ በህዳር 2022 በህወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል በትግራይ ያለውን ጦርነት ለማቆም የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት አካል ሆኖ ከተፈረመው ስምምነት ውስጥ አንዱ እንደሆነ
  • ጊዜያዊ መንግስት ባለመኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ርዳታ በሚሹበት ትግራይ ሰብዓዊ ርዳታ እያስተጓጎለ ነው ሲሉ የእርዳታ ሰራተኞች መግለጻቸው
  • በተመሳሳይ መልኩ ለሲቪል ሰርቫንቱና ለህክምና ባለሙያዎች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው የእርዳታ ድርጅቶችም ግልፅ ጣልቃ ገብነት እንደሌላቸው
  • ጊዜያዊ አስተዳደሩን የተቋቋመው በኢትዮጵያ ፓርላማ የላይኛው ምክር ቤት ሲሆን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ተወካይ አቶ ጌታቸው ረዳን በጊዜያዊ አስተዳደርነት በመሾም እንደሆነ  የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው

ሊንክ  https://www.aljazeera.com/news/2023/3/23/ethiopia-says-tigray-interim-administration-set-up-as-part-of-peace-plan

Guardian

  • ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የህወሓት ባለስልጣን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊ አደረገዉ የሚል ዘገባ ነዉ።

 የተነሱ ነጥቦች

  • የኢትዮጵያ መንግስት በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ  ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣንን በጊዜያዊ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መሾሙን የምገለጸ።
  • ይህ ማስታወቂያ በህዳር 2022 በአማፂያኑ እና በፌደራል መንግስት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለማጠናከር ይረዳል ባለው እርምጃ ፓርላማው ህወሓትን ከአሸባሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ ካስወገደ ከአንድ ቀን በኋላ እንደሆነ።
  • በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሲቆጣጠር የነበረው ህወሓት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከጀመረ ከስድስት ወራት በኋላ በግንቦት 2021 በአሸባሪነት እንደተፈረጀ ሚያስታዉስ።
  • በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ በተፈረመው የኖቬምበር የሰላም ስምምነት ውል መሰረት ህወሓት ትጥቅ ለማስፈታት ሲምምነት እንደ ነበረ።
  • ከስምምነቱ በኋላ ለትግራይ የምግብ፣ የነዳጅ፣ የጥሬ ገንዘብ እና የመድኃኒት እጦት መጠነኛ የመሠረታዊ አገልግሎቶች እና የዕርዳታ አቅርቦቶች እንደገና መጀመሩን

ሊንክ  –  https://www.theguardian.com/world/2023/mar/23/ethiopia-pm-appoints-tplf-official-head-o

   VOA

  • የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተፈጸሙ ጥሰቶች መመርመር የሚያብራራ ነው።

  የተነሱ ነጥቦች

  • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ከሁለት አመት በላይ በዘለቀው የትጥቅ ግጭት የተፈጸሙ ጥሰቶች ካልተመረመሩ እና አጥፊዎች በህግ እስካልተጠየቁ ድረስ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ሰላም ዘላቂ እንደማይሆን
  • በማክሰኞ ለት ማለትም መጋቢት 21 ,2023 በጄኔቫ ላይ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የቅርብ ጊዜ ሪፖርቱን ያቀረበው ሶስት አባላት ያሉት የዩናይትድ ኢስቴት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ባለሞያዎች ኮሚሽን፣ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተፈጠረውን ጦርነት ያቆመውን የሰላም ስምምነት በደስታ መቀበሉን።
  •  “በተለይ ለሰብአዊ መብቶች፣ ለሲቪሎች ጥበቃ፣ ያልተገታ የሰብአዊ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት ቁርጠኝነትን እንቀበላለን” የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሀመድ ቻንዴ ኦትማን መናገራቸዉን።
  • አክሎም ሊቀመንበሩ ለሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በህዳር 2020 ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙትን ጥሰቶች ክብደት እና መጠን መዘንጋት እንደሌለበት ማስታወሳቸዉን
  • ይህ አመለካከት ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በዓለም ዙሪያ ስለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አመታዊ ዘገባ ላይ ተስተጋብቷል
  • የኢትዮጵያ መንግስት ለሁለት አመታት በዘለቀው የትግራይ ጦርነት ሁሉም ወገኖች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚለውን የአሜሪካ መግለጫ  ውድቅ በማድረግ መግለጫውን “አስጨናቂ” ማለቱም ተነሷል
  • በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጄኔቫ ላይ፣ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፀጋብ ክበበው ዳካ ኮሚሽኑ የሰላም ስምምነቱን ሊያናጋ የሚችል “አጋጭ መረጃ” እንዳይጠቀሙ ማለታቸዉ

ሊንክ https://www.voanews.com/a/rights-experts-violations-in-ethiopia-must-be-investigated-to-ensu

  ZAWYA

  • ኢትዮጵያ የህወሓት ከፍተኛ አመራርን የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አድርጋ ሾመች የሚል ነው።

 የተነሱ ነጥቦች

  • የኢትዮጵያ መንግስት በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣን ለትግራይ ጊዜያዊ መንግስት መሪ አድርጎ መሾሙን
  • ይህ ኩነት ፓርላማው ወያኔን ከአሸባሪ ድርጅቶች ይፋዊ ዝርዝር ውስጥ ካስወገደ ከአንድ ቀን በኋላ ሲሆን ይህ እርምጃ በህዳር 2022 በአማፂያኑ እና በፌደራል መንግስት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ለማጠናከር ይረዳል ብሏል።
  • ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አድርጎ እንደሾሙ
  • በስምምነቱ መሰረት ህወሓት ትጥቅ ለማስፈታት የተስማማው በጦርነቱ ወቅት ከውጪው አለም ተቋርጦ የነበረውን ትግራይን ለመመለስ እንደነበር
  • ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለትግራይ ከፍተኛ የምግብ፣ የነዳጅ፣ የጥሬ ገንዘብ እና የመድኃኒት እጦት ወድቃ የነበረችዉ የመሠረታዊ አገልግሎት እና የእርዳታ አቅርቦት መመቻችቱን የሚገልጹ ነጥቦች ዋና ዋና ነጥቦች እንደሆኑ

ሊንክ  –  https://www.zawya.com/en/world/africa/ethiopia-appoints-senior-tplf-official-as-head-of-tigra

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *