የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሰኔ 17 | 2014 ዓ.ም – June 24 |2022
voa
- በአፋር ክልል ዜጎች በምግብና በመጠለያ እጦት መቸገራቸውንና ትኩረት እንደሚሹ ለማሳየት የተጻፈው ነው።
- በኢትዮጵያ አፋር ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች በምግብ እና በመጠለያ እጦት ምክንያት ካምፖችን ለቀው እየወጡ መሆኑናቸውን ነው የጻፈው።
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ ነበሩበት ቤት መመለስ ቢጀምሩም ነገር ኝ እርዳታን እያፈላለገ እንደሆነ መግለጹንም ነው የጻፈው።
Africa intelligence
- ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ግድብ ላይ እየተነጋገረች ባለችበት ወቅት ግብፅ ሱዳንን ፍርድ ቤት ማቅረቧን መቀጠሏን ዘገባው ጽፏል ።
- ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ የህዳሴውን ግድብ ሙሌት ለማድረግ በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት፣ የግብፅ ዲፕሎማሲያዊ ቡድን ሱዳን ከጎኗ እንድትቆም ለማድረግ እርምጃ እየወሰደች መሆኗን ዘገባው ለማሳየት የሞከረ ነው። ይህ የሚያመለክተው ግብጽ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የኤሌክትሪክ ንግድ ትሥሥርን ጨምሮ መልካም ግንኙነትን ልትመሠርት እንደምትችል በ፣እስጋቷና ያንን ለማበላሸት ሱዳንን ከጎኗን እንድትቆም የማስገደድ ያህል ጠንካራ ግፊት እያደረገች እንዳለች የሚያሳይ ነው።
Press tv
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብት ክንፍ ሃላፊ በኢትዮጵያ የጅምላ ግድያ ላይ ገለልተኛ “አፋጣኝ፣ ገለልተኛ እና ጥልቅ” ምርመራ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን መጠየቃቸውን ነው የሚያሳየው።
- ሰኔ 18 አ.ኤ.አ በኦሮሚያ ክልል በተፈፀመው ጥቃት ታጣቂዎች ቶሌ ወረዳ ላይ ወርደው ንጹሀን ዜጎች ላይ በዘፈቀደ መተኮሳቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን የዐይን ምስክሮች መረጃ መስጠታቸውን በማካተት ነው የጻፈው።
- ዘገባው አክሏ በኦሮሚያና አጎራባች ጋምቤላ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በንፁሀን ዜጎች ላይ አሰቃቂ እና ኢ-ሰብአዊ ግፍ በ ሸኔ መፈጸሙን በግልጽ አስቀምጧል።
- “የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በጥቃቱ ላይ በፍጥነት ምርመራ መጀመሩን እንዲያረጋግጡ እና ተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው እውነት፣ ፍትህ እና ካሳ የማግኘት መብት እንዳላቸው እንዲያረጋግጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ ጥፋተኞችን ተጠያቂ በማድረግም ጭምር ” ሲሉ ወ/ሮ ባችሌት መናገራቸውን ጽፎ ጉዳዩ በዓለማቀፍ ደረጃ ትኩረት ማግኘት መቻሉን ነው ያሳየው።