የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
![](https://ethiopiantruth.com/wp-content/uploads/2023/02/Y4.png)
የካቲት 4፣ | 2015 ዓ.ም – Feb. 12 | 2023
Reuters
- በኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ መቃቃር ወደ ብጥብጥ ከተቀየረ በኋላ የማህበራዊ ሚዲያ የኢንተርኔት ግንኙነት እንደተገደበ የሚገልጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ተደራሽነት መዘጋቱን የኢንተርኔት ተቆጣጣሪው ኔትብሎክስ እንዳስታወቀ።
- ህዝባዊ ተቃውሞው በኦሮምያ ክልል የተቀሰቀሰው ባለፈው ወር ሶስት የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች ሊቀ ጳጳስ እንደሆኑ በማወጅ የራሳቸው አዲስ ሲኖዶስ በማቋቋም እንደሆነ
- ይህን ድርጊት አንዳንድ ተቃዋሚዎች እርምጃቸውን ሲቃወሙ ሌሎች ደግሞ እንደደገፉ የሚያነሱት ዋና ዋና የመረጃው ነጥቦች ናቸው።
Jurist
- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ወደ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተመጣጣኝ አይደለም ማለቱን የተነተን ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አርብ ዕለት ከሀገሪቱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በከዱ ሰዎች በሀይማኖቱ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ኢፍትሐዊ ድርጊት እንደሆነ
- በኮሚሽኑ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደው ሃይል ያልተመጣጠነ ነው ሲል ገልጾ እየታየ ያለው ግጭት የእምነት ነፃነትን በሚያጎለብት መንገድ ሊፈታ እንደሚችል መግለጹ
- ከቤተክርስቲያኑ ጋር በመተባበር ብዚዎች ወደ አደባባይ በመውጣታቸው በተፈጠሩ አለመግባባቶች ሰዎች እንደሞቱ
- ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ መንግስት የተሳሳቱ መረጃዎችን ሊሰራጭ ስለሚችል የማህበራዊ ሚዲያ ጦርነቱን ሊያባብሰው ከሚችለው አደጋዎችና እርምጃዎች እንዲጠነቀቅ መምከሩ
- ኮሚሽኑ መንግስት በግጭቱ ላይ የሚያካሂዱትን መደበኛ ምርመራ ከማድረግ በተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎችን እንዲያማክር እንደጠየቀ የሙሉና የመሳሰሉት የመረጃዎች ይዘት ሀሳቦች ናቸው።