የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ሰኔ 13 | 2014 ዓ.ም – June 20 |2022
Reuters
- የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ቅዳሜ ረፋድ ላይ በሰጠው መግለጫ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨው ቪዲዮ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በታህሳስ 2021 ቢያንስ 30 ከህግ አግባብ ውጭ ግድያ ሲፈጽሙ የሚያሳይ መሆኑን የሚገልጽ ነው።
- ከ አርብ ጀምሮ በሰፊው የተሰራጨው ቪዲዮው የሰራዊት የውጊያ ልብስ የለበሱ ሰዎች በገጠር መንገድ ዳር ከቆሙት የጭነት መኪናዎች ላይ እያወዱ ተኩሰው ሲገድሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ጋር በማያያዝ በትንሹ 30 ሰዎች ገድለዋል” በሚል ከሠሞኑ ተመሣሣይ የሆነ ዘገባን እያስተጋቡ እንደሆነ የሚገልጽ ዘገባ ነው የጻፈው።
- ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
The Guardian
- ከ200 በላይ የአማራ ተወላጆች በአሸባሪዎች መገደላቸውንና በድርጊቱም ባሸባሪነት የተፈረጁ ቡድኖች እንደሚጠረጠሩም የሚዘግብ ነው።
- በኦሮሚያ ክልል ተገድለዋል የተባሉ እነዚህ ንጹሀን ዜጎች የተገደሉት አሸባሪ ተብለው በተፈረጁ ታጣቂ ሀዮሎች እንድሆነም ባካባቢው ያሉ እማኞች እንደሚናገሩም መረጃ እግኝቻለውሁ ነው የሚለው።
- ግድያውም ሊቆም የቻለበት ምክንያት ለመግለጽ ምየፌደራል ጦር ሃይሎች አሁን ደርሰውልናል ነገር ግን መንግስት ስፍራውን ለቆ ከወጣ ሊቀጥሉ ይችላሉ ብለው እንደሚሰጉ በመግለጽ መግስት ሁኔታዉን መቆጣጠር እንደሚችልና ዜጎችም በምንግስት የጽጥታ ሀይሎች ላይ እምነት እንዳላቸው የሚገልጽ መረጃንም አካቷል።
- ቢሆንም ግን መንግስት ለጊዜው እንጅ ችግሩን ለዘላቂነት መፍታት አለመቻሉንም ለማሳየት ሞክሯል።
- ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
Al Jazeera
- ይህ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸውን እማኞች አንደተናገሩ ነው የጻፈው።
- በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በተፈፀመ ጥቃት ከ100 በላይ የሚሆኑ አብዛኞቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደተገደሉ ነው የጻፈው።
- ይህም የእማኞች ምስክርነት በሚል እማኞቹም የኦነግ ሸኔን ታጣቂዎችን እንዳደረጉት የሚያሳይ ጥቆማ መስጠታቸውንም ነው የጻፈው።
- የኦሮሚያ ክልል መንግስት ጥቃቱን ማረጋገጡን ቢያረጋግጥም የሟቾችን ቁጥር በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንዳልሰጠ ጽፏል።
- የፌደራል መንግሥት አስተያየት እንዲሰጥ ማግኘት አለመቻሉንም ለማሳየት ሞኽሯል ።
- ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
ሊንክ https://www.aljazeera.com/news/2022/6/20/hundreds-killed-in-ethiopias-oromo-region