የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ጥር 24 ፣ | 2015 ዓ.ም – Feb. 1 | 2023
Military Africa
- ኢትዮጵያ የሮኬት እና የመድፍ አቅምን እንዳሳድጋለች የሚገልጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት በሩቅ የሚደርሱ ስጋቶችን ለማየትና ለመምታት በረዥም ርቀት የጦር መሣርያዎች እንዳሉት
- ይህ ሠራዊት የምስራቅ አፍሪካ ጀግና እንደሆነና ሠራዊቱ ጊዜው የምሥራቅ አፍሪካ ክልላዊ ቀውሶችን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም የመድፍ እና የሮኬት አቅሞችንና ሌሎች ስትራቴጂካዊ መሳሪያዎችን ማጠናከሩን መቀጠሉን
- ኢትዮጵያ ወታደራዊ የማጥቃት አቅሟን በእጅጉ ለማስፋት እና የየውጭ ጠላቶቿንም ለመከላከል በእጅጉ በመዘጋጀት ላይ የምትገኘው አሁን እጅግ ዘመናዊ መሣርያዎች መታተቅ እንደጀመረች
- ኢትዮጵያ ያቀደቻቸውና እያሳካች ካለቻቸው ውጥኖች መካክል የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና የረዥም ርቀት (የሚመሩ) ሮኬቶችን መግዛት እንደነበርና ሁለቱ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው እንዳልነበር።
- ኢትዮጵያ ረዣዥም ርቀቶች ቻይናውያን ሰራሽ ግማሽ ደርዘን PHL-03 300 ሚሜ ኤምአርኤልኤስ፣ ኤ-200 የሚመራ ሮኬት መድፍ (GRA) ሲስተሞች እና ኤም-20 የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎች (SRBMs)ን መግዛቷን
- እንደነዚህ ያሉት የጦር መሳሪያዎች ከ150 ኪ.ሜ (93 ማይል) እስከ 300 ኪ.ሜ (186 ማይል) መካከል ያለው ርቀት መወንጨፍ እንደሚችሉ
ሊንክ – https://www.military.africa/2023/02/ethiopias-improves-rocket-and-artillery-forces-
All Africa
- የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት የተጠናከረ ሲሄድ የትግራይ እርዳታ ተደራሽነት እንደሚሻሻል የሚተነትን ነው።
የተነሱነጥቦች
- የሠላም ስምምነቱ ከተፈረመ ከሶስት ወራት ገደማ በኋላ ለክልሉ ነዋሪዎች ነጻነትን እያጎናጸፋቸው እንደመጣና በአብዛኛው ሰብአዊ እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ክልሉ እንደገባና ለተቸገሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እየደረሰ እንደሚገኝ
- በደቡብ አፍሪካ በተፈረመው ስምምነት መሰረት ባለፉት ሳምንታት የህወሓት ሃይሎች እጃቸው ላይ የነበሩ ከባድ መሳሪያዎችን እንዳስረከቡ
- የኤርትራ ወታደሮችም የስምምነቱ አካል እንደሆኑና በመሆኑም ከትግራይ ለቀው እየወጡ ነው ሲሉ የትግራይ ነዋሪዎች ለሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች መንገራቸው
- ሆኖም የኤርትራ ጦር በድንበር ላይ እንደሚቆይ እና እስካሁንም ከኢትዮጵያ ምድር ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣ አሜርካ መግለጿን የሚታወስ እንደሆነ
ሊንክ – https://allafrica.com/stories/202302010036.html
Responsible state craft
- በአሌክስ ዲዋል የተጻፈ፣ ከትግራይ ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያ በአደገኛ የፖለቲካ አለመረጋጋት ሁኔታ ውስጥ ግብታ እንደምትገኝ ነው የሚገልጸው።
የተነሱነጥቦች
- አሜሪካ እና ሌሎች ለጋሾች የአብይን የግል የፖለቲካ አጀንዳ በሚያጠናክሩ መንገዶች ሀገሪቱን ከችግር ለማዳን ከሚያደርጉትን ጥረቶች መቆጠብ እንዳለባቸው
- መንግስት ዜጎችን ያላማከሉ በቤተመንግስትና በፓርቲው ጽ/ቤቶች ጸረ ህዝብ የተቀነባበሩ ሴራዎችን እነደሚሠራ
- የኢትዮጵያ ፖለቲካ የማይረጋጋ እንደሆነና ሁሌች ችግሮች እንደሚኖሩት
- በጦርነቱ በትግራይ ውስጥ የዜጎች ሞት የተሻለው ግምት ከ500,000 በላይ ሲሆን ባብዛኛው በረሃብና በበሽታ እንደሆነ
- የህወሓት አመራር ለትግራይ ህዝብ መራብና ሞት ሲል ተገዶ ወደ ሠላም እንደመጣ
- የኢትዮጵያ ጦር በጦርነቱ 254,000 ሞት እንደደረሰበት፣
- በኬንያ ናይሮቢ የተፈረመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የተደረገው የሰላም ስምምነት ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ሳይሆን የኢትዮጵያን ነባሩን ህገመንግስትን ለማስከበት የተቀረጸ እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://responsiblestatecraft.org/2023/01/31/ethiopia-dangerously-adrift-after-tigray-war/