የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጥር 20 ፣ | 2015 ዓ.ም – Jan 28 | 2023
The Star
- በኢትዮጵያ ግጭት ወደተከሰተ የትግራይ ክልል በጦርነት አማካኝነት ተቋርጦ የነበረው የህዝብ ትራንስፖርት ሊቀጥል እንደሆነ የሚያስረዳ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ መንግስት ግጭት ወደ ተከሰተብት ሰሜናዊ ምስራቅ ትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የህዝብ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን እንዳሳወቀ
- በዚህም መሠረት ከአዲስ አበባ ከተማ የየብስ ትራንስፖርት እንዲጀመር የኢትዮጵያ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለህዝብ ማመላለሻ ማህበራት መመሪያ መላኩን እንዳሳወቀ
- አገልግሎቱ በክልሉ ርዕሰ መዲና መቀሌ፣ አክሱምና ሽሬ እና ሌሎች አካባቢዎች እንደሚጀመርም መገለጹ
- በቅርቡም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ክልሉ ተቋርጦ የነበረውን በረራ እንደጀመረውም የሚታወስ መሆኑ
ሊንክ – https://www.thestar.com.my/news/world/2023/01/28/ethiopia-to-resume-public-
AFP
- ያኔት ድንቁ በተሰኝች አንዲት አርቲስት የተጻፈ አንድ የፌስቡክ ፖስት ከ AFP ጋር ተደረገ የተባለው ነገር ግን በሌለው ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ ለመሳብ የሞከረ በሚል የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- መረጃው አንድ የAFP ጋዜጠኛ ወደ ኦሮሚያ ክልል በማምራት የኦንግ ሸኔን መሪ ጃል ገመቹ አቦዬ የተባለውን ቃለ መጠይቅ እንዳደረገለት በማስመሰል የተጻፈ እንደሆነ
- ነገር ግን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የኦነግ ሽኔን ሃላፊ ጃል ገመቹን ቃለመጠይ እንዳላደረጉለት መግለጹ
- ተመሳሳይ የሆኑ ልጥፎች በፌስቡክ በመጻፍ ብዙ ችግሮች በኢትዮጵያ ተፈጥረው እንደነበር መገለጹ የሚሉት በጽሁፉ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://factcheck.afp.com/doc.afp.com.337W6F9